“ኀይል የሌለውን ምንኛ ረዳኸው! ደካማውንስ ምንኛ አዳንኸው!
እኩለ ቀንም ላይ ኤልያስ፣ “ድምፃችሁን ከፍ አድርጋችሁ ጩኹ እንጂ፤ አምላክ አይደለም እንዴ! ምናልባት በሐሳብ ተውጦ ወይም ሥራ በዝቶበት፣ አልያም በጕዞ ላይ ይሆናል፤ ተኝቶም ከሆነ ቀስቅሱት” እያለ ያፌዝባቸው ጀመር።
“በርግጥ ሰው ማለት እናንተ ናችኋ! ጥበብም ከእናንተ ጋራ ትሞታለቻ!
ኢዮብም እንዲህ ሲል መለሰ፤
ጥበብ የሌለውን ምንኛ መከርኸው! ታላቅ ዕውቀትንስ ምንኛ ገለጥህለት!
ሁላችሁ ይህን አይታችኋል፤ ታዲያ፣ ይህ ከንቱ ንግግር ምንድን ነው?
“አሁንም ተስፋ አደርግ ዘንድ ብርታቴ፣ እታገሥስ ዘንድ አለኝታዬ ምንድን ነው?
የድንጋይ ጕልበት አለኝን? ሥጋዬስ ናስ ነውን?
ያልተሳካልኝ ሰው ነኝና፣ ራሴን ለመርዳት ምን ጕልበት አለኝ?
የቅንነት ቃል ምንኛ ኀያል ነው! የእናንተ ክርክር ግን ምን ፋይዳ አለው?
በእርጅናዬ ዘመን አትጣለኝ፤ ጕልበቴም ባለቀበት ጊዜ አትተወኝ።
ዕውቀት ለማግኘት እግዚአብሔር ማንን አማከረ? ትክክለኛውንስ መንገድ ማን አስተማረው? ዕውቀትን ያስተማረው፣ የማስተዋልንም መንገድ ያሳየው ማን ነበር?