ድኾችን ከመንገድ ያስወግዳሉ፤ የምድሪቱም ችግረኞችን ይሸሸጋሉ።
ቀኑ ሲመሽ፣ ነፍሰ ገዳይ ይነሣል፤ ችግረኞችንና ድኾችን ይገድላል፤ በሌሊትም እንደ ሌባ ያደባል፤
ለርዳታ የሚጮኸውን ችግረኛ፣ ድኻ አደጉንም ታድጌአለሁና።
ለድኾች አባት፣ ለባይተዋሩ ተሟጋች ነበርሁ።
በመከራ ውስጥ ላሉት አላለቀስሁምን? ለድኾችስ ነፍሴ አላዘነችምን?
“ለድኻ የሚያስፈልገውን ከልክዬ ከሆነ፣ ወይም የመበለቲቱን ዐይን አፍዝዤ ከሆነ፣
በልብስ ዕጦት ሰው ሲጠፋ፣ ወይም ዕርቃኑን ያልሸፈነ ድኻ አይቼ፣
ድኻውንና ችግረኛውን፣ ልቡም የቈሰለውን፣ እስከ ሞት አሳደደ እንጂ፣ ምሕረት ያደርግ ዘንድ አላሰበምና።
ብፁዕ ነው፤ ለድኾች የሚያስብ፤ እግዚአብሔር በክፉ ቀን ይታደገዋል።
ድኾችን የሚያስጨንቅ ፈጣሪያቸውን ይንቃል፤ ለተቸገሩ የሚራራ ሁሉ ግን አምላክን ያከብራል።
ሀብቱን ለማካበት ድኻን የሚበድል፣ ለባለጠጋም ስጦታ የሚያቀርብ፣ ሁለቱም ይደኸያሉ።
ጻድቃን ድል ሲነሡ ታላቅ ደስታ ይሆናል፤ ክፉዎች ሥልጣን ሲይዙ ግን ሕዝብ ይሸሸጋል።
ክፉዎች ሥልጣን በሚይዙ ጊዜ ሕዝብ ይሸሸጋል፤ ክፉዎች በሚጠፉበት ጊዜ ግን ጻድቃን ይበዛሉ።
ድኾችን ከምድር፣ ችግረኞችንም ከሰው ዘር መካከል ለማጥፋት፣ ጥርሳቸው ሰይፍ የሆነ፣ መንጋጋቸውም ካራ የሆነ አሉ።
የድኾችን መብት ለሚገፍፉ፣ የተጨቈነውን ሕዝቤን ፍትሕ ለሚያዛቡ፣ መበለቶችን ለሚበዘብዙ፣ ወላጅ የሌላቸውን ልጆች ለሚመዘብሩ ወዮላቸው!
ድኻውንና ችግረኛውን ቢጨቍን፣ በጕልበት ቢቀማ፣ በመያዣነት የወሰደውን ባይመልስ፣ ወደ ጣዖታት ቢመለከት፣ አስጸያፊ ተግባራትን ቢፈጽም፣
አባቱ ግን የሰውን መብት ስለ ደፈረ፣ ወንድሙን በጕልበት ስለ ቀማና በሕዝቡ መካከል የማይገባውን ስላደረገ በገዛ ኀጢአቱ ይሞታል።
በምድሪቱ የሚኖረው ሕዝብ ይቀማል፤ ይዘርፋል፤ ፍትሕ በማጕደልም ድኻውንና ችግረኛውን ይጨቍናል፤ መጻተኛውንም ይበድላል።
የችግረኞችን ራስ፣ በምድር ትቢያ ላይ ይረግጣሉ፤ ፍትሕንም ከጭቍኖች ይነጥቃሉ፤ አባትና ልጅ ከአንዲት ሴት ጋራ ይተኛሉ፤ እንዲህም እያደረጉ ቅዱስ ስሜን ያረክሳሉ።
እናንተ በሰማርያ ተራራ የምትኖሩ የባሳን ላሞች፤ ድኾችን የምትጨቍኑና ችግረኞችን የምታስጨንቁ፣ ባሎቻችሁንም፣ “መጠጥ አቅርቡልን” የምትሉ ሴቶች ይህን ቃል ስሙ፤