ነገር ግን እግዚአብሔር ኀያላንን በኀይሉ ጐትቶ ይጥላል፤ ቢደላደሉም የሕይወት ዋስትና የላቸውም።
ካህናትን ከክህነታቸው ያዋርዳል፤ ለዘመናት የተደላደሉትንም ይገለብጣል።
ባጋጠመው ሁኔታ የምዕራብ ሰዎች ይደነግጣሉ፤ የምሥራቅም ሰዎች በፍርሀት ይዋጣሉ።
ጥበቡ ጥልቅ፣ ኀይሉም ታላቅ ነውና፤ እርሱን ተቃውሞ ያለ አንዳች ጕዳት የሄደ ማን ነው?
የምድር ነገሥታት ከርሷ ጋራ አመነዘሩ፤ የምድር ነዋሪዎችም በዝሙቷ የወይን ጠጅ ሰከሩ።”