ሰዎች ድንበር ይገፋሉ፤ የሰረቁትን መንጋ ያሰማራሉ።
ሳባውያን ጥቃት አድርሰውባቸው ይዘዋቸው ሄዱ፤ አገልጋዮቹንም በሰይፍ ገደሉ። እኔም ብቻዬን አመለጥሁ፤ ልነግርህም መጣሁ።”
እርሱም እየተናገረ ሳለ፣ ሌላ መልእክተኛ መጥቶ፣ “ከለዳውያን በሦስት ቡድን መጥተው ጥቃት አደረሱ፤ ግመሎችህንም ይዘው ሄዱ፤ አገልጋዮቹን በሰይፍ ገደሉ፤ እኔም ብቻዬን አመለጥሁ፤ ልነግርህም መጣሁ” አለው።
ድኾችን በመጨቈን ባዶ አስቀርቷቸዋልና፣ ያልሠራውንም ቤት ነጥቋል።
“ዕርሻዬ በእኔ ላይ ጮኻ ከሆነ፣ ትልሞቿ ሁሉ በእንባ ርሰው እንደ ሆነ፣
ከእሾኽ መካከል እንኳ አውጥቶ፣ ራብተኛ ሰብሉን ይበላበታል፤ ጥማተኛም ሀብቱን ይመኝበታል።
የቀድሞ አባቶችህ ያስቀመጡትን፣ የጥንቱን የወሰን ምልክት አታፋልስ።
የጥንቱን የወሰን ምልክት አታፋልስ፤ አባት የሌላቸውንም ልጆች መሬት አትግፋ፤
የይሁዳ መሪዎች፣ የወሰን ድንጋዮችን እንደሚነቅሉ ሰዎች ናቸው፤ እንደ ጐርፍ ውሃ፣ ቍጣዬን በላያቸው ላይ አፈስሳለሁ።
አምላክህ እግዚአብሔር እንድትወርሳት በሚሰጥህ ምድር ውስጥ ለአንተ በሚተላለፍልህ ርስት ላይ የቀድሞ ሰዎች ያስቀመጡትን የባልንጀራህን የድንበር ምልክት አታንሣ።
“የባልንጀራውን የድንበር ድንጋይ ከቦታው የሚያንቀሳቅስ የተረገመ ይሁን።” ሕዝቡም ሁሉ፣ “አሜን!” ይበል።