የሚመልስልኝ ቃል ምን እንደ ሆነ ባወቅሁ ነበር፤ የሚለኝንም ባስተዋልሁ ነበር።
እግዚአብሔርን እንዲህ እለዋለሁ፤ በምን ላይ እንዳልተስማማን ንገረኝ እንጂ አትፍረድብኝ።
ጕዳዬን በፊቱ አቀርብ ነበር፤ አፌንም በሙግት እሞላው ነበር።
በታላቅ ኀይሉ ከእኔ ጋራ ይሟገት ይሆን? አይደለም፤ ይልቁን ያደምጠኛል።