ጻድቃንም የእነዚያን ጥፋት አይተው ይደሰታሉ፤ ንጹሓንም እንዲህ ብለው ያፌዙባቸዋል፤
ቅኖች በዚህ ነገር ይደነግጣሉ፤ ንጹሓንም በዐመፀኞች ላይ ይነሣሉ።
መዓት ወርዶ ድንገት ሰው ሲጨርስ፣ በንጹሓን መከራ ይሣለቃል።
ልበ ቅኖች ይህን አይተው ሐሤት ያደርጋሉ፤ ጥመትም ሁሉ አፏን ትዘጋለች።
ስለ ፍርድህ፣ የጽዮን ተራራ ሐሤት ታድርግ፤ የይሁዳ መንደሮችም ደስ ይበላቸው።
ጻድቃን ይህን አይተው ይፈራሉ፤ እንዲህ እያሉም ይሥቁበታል፤
ጻድቃን በቀልን ባዩ ጊዜ ደስ ይላቸዋል፤ እግራቸውንም በግፈኞች ደም ይታጠባሉ።
ጻድቅ በእግዚአብሔር ደስ ይበለው፤ እርሱንም መጠጊያ ያድርገው፤ ልበ ቅኖችም ሁሉ ደስ ይበላቸው።
እግዚአብሔር ሆይ፤ ስለ ፍርድህ፣ ጽዮን ሰምታ ደስ አላት፤ የይሁዳም ሴት ልጆች ሐሤት አደረጉ።
ጻድቃን ሲሳካላቸው ከተማ ደስ ይላታል፤ ክፉዎች ሲጠፉ እልልታ ይሆናል።
“ሰማይ ሆይ፤ በርሷ ላይ ሐሤት አድርግ! ቅዱሳን፣ ሐዋርያትና ነቢያትም ሐሤት አድርጉ! በእናንተ ላይ ባደረሰችው ነገር እግዚአብሔር ፈርዶባታልና።”