ስለዚህ ነገር ባሰብሁ ቍጥር እደነግጣለሁ፤ ሰውነቴም በፍርሀት ይንቀጠቀጣል።
ንጹሕ አድርገህ እንደማትቈጥረኝ ስለማውቅ፣ መከራዬን ሁሉ እፈራለሁ።
ሥጋዬ አንተን በመፍራት ይንቀጠቀጣል፤ ፍርድህንም እፈራለሁ።
ፍርሀትና እንቅጥቃጤ መጣብኝ፤ ሽብርም ዋጠኝ።
አምላክ ሆይ፤ አንተን ባሰብሁ ቍጥር ቃተትሁ፤ ባወጣሁ ባወረድሁም መጠን መንፈሴ ዛለች። ሴላ
እኔ ከልጅነቴ ጀምሮ ችግረኛና ለሞት የተቃረብሁ ነበርሁ፤ መዓትህ አሠቃየኝ፤ ግራም ተጋባሁ።
ማቅ ይለብሳሉ፤ ሽብርም ይውጣቸዋል። ፊታቸው ኀፍረት ይለብሳል፤ ራሳቸውም ይላጫል።
እኔ ሰማሁ፤ ልቤም ደነገጠብኝ፤ ከንፈሬ ከድምፁ የተነሣ ተንቀጠቀጠ፤ ፍርሀት እስከ ዐጥንቴ ዘልቆ ገባ፤ እግሬም ተብረከረከ፤ ሆኖም በሚወርረን ሕዝብ ላይ እስኪመጣ ድረስ፣ የጥፋትን ቀን በትዕግሥት እጠባበቃለሁ።