ወደ መቃብር ይወስዱታል፤ ለመቃብሩም ጠባቂ ይደረግለታል።
ተግባሩን ፊት ለፊት የሚነግረው ማን ነው? የእጁንስ ማን ይሰጠዋል?
የሸለቈው ዐፈር ምቹ ይሆንለታል፤ ሰው ሁሉ ይከተለዋል፤ ስፍር ቍጥር የሌለው ሕዝብ በፊቱ ይሄዳል።
እንደ በጎች ለሲኦል የተዳረጉ ናቸው፤ ሞትም እረኛቸው ይሆናል፤ ቅኖች በማለዳ ይገዟቸዋል፤ አካላቸው ከክብር ቤታቸው ርቆ፣ በሲኦል ይፈራርሳል።
ነገር ግን እንደ ማንኛውም ሰው ትሞታላችሁ፤ እንደ ማንኛውም ገዥ ትወድቃላችሁ።”
“ይህም ድኻ ሞተ፤ መላእክትም ወደ አብርሃም ዕቅፍ ወሰዱት። ሀብታሙም ሰው ደግሞ ሞቶ ተቀበረ።