መንገደኞችን አልጠየቃችሁምን? የነገሯችሁንስ ነገር በጥሞና አላዳመጣችሁምን?
እናንተ፣ ‘የትልቁ ሰው ቤት፣ ኀጢአተኛውም የኖረበት ድንኳን የት አለ?’ አላችሁ፤
ክፉ ሰው በመቅሠፍት ቀን እንደሚጠበቅ፣ በቍጣም ቀን እንደሚተርፍ አታውቁምን?
መንገድ ዐላፊዎችም፣ “የእግዚአብሔር በረከት በእናንተ ላይ ይሁን፤ በእግዚአብሔር ስም እንባርካችኋለን” አይበሉ።