ልጆቻቸውን እንደ በግ መንጋ ያሰማራሉ፤ ሕፃናታቸውም ይቦርቃሉ።
ኰርማቸው ዘሩ በከንቱ አይወድቅም፤ ያስረግዛል፤ ላማቸውም ሳትጨነግፍ ትወልዳለች።
በከበሮና በክራር ይዘፍናሉ፤ በዋሽንትም ድምፅ ይፈነጫሉ።
ድኾችን ግን ከጭንቀታቸው መዝዞ አወጣቸው፤ ቤተ ሰባቸውንም እንደ በግ መንጋ አበዛ።