“ክፋት በአፉ ውስጥ ቢጣፍጥ፣ ከምላሱም በታች ቢደብቀው፣
ሴቲቱ የዛፉ ፍሬ ለመብል መልካም፣ ለዐይን የሚያስደስትና ጥበብንም ለማግኘት የሚያጓጓ እንደ ሆነ ባየች ጊዜ፣ ከፍሬው ወስዳ በላች፤ ከርሷም ጋራ ለነበረው ለባሏ ሰጠችው፤ እርሱም በላ።
ከዚያም ዳዊት፣ “እንግዲያውስ ዛሬ እዚህ ዕደርና ነገ አሰናብትሃለሁ” አለው። ስለዚህ ኦርዮን በዚያ ዕለትና በማግስቱም እዚያው ኢየሩሳሌም ቈየ።
ታዲያ፣ ክፋትን እንደ ውሃ የሚጠጣ፣ አስጸያፊና ርኩስ ሰውማ እንዴት ይታመን!
አፉ መርገምን፣ ቅጥፈትንና ግፍን የተሞላ ነው፤ ሽንገላና ክፋት ከምላሱ ሥር ይገኛሉ።
ምናምንቴ ምስክር በፍትሕ ላይ ያፌዛል፤ የክፉዎችም አፍ በደልን ይሰለቅጣል።
ሰው በማጭበርበር ያገኘው ምግብ ይጣፍጠዋል፤ በመጨረሻ ግን አፉን ኰረት ሞልቶት ያገኘዋል።
አንተ ወጣት በወጣትነትህ ጊዜ ደስ ይበልህ፤ በወጣትነትህም ዘመን ልብህ ደስ ያሰኝህ፤ የልብህን መንገድ፣ ዐይንህ የሚያየውንም ሁሉ ተከተል፤ ነገር ግን ስለ እነዚህ ነገሮች ሁሉ፣ አምላክ ወደ ፍርድ እንደሚያመጣህ ዕወቅ።
ክፋትሽ ቅጣት ያስከትልብሻል፤ ክሕደትሽም ተግሣጽ ያመጣብሻል፤ እግዚአብሔር አምላክሽን ስትተዪ፣ እኔንም መፍራት ችላ ስትይ፣ ምን ያህል ክፉና መራራ እንደሚሆንብሽ አስቢ፤ እስኪ አስተውዪ፤” ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር።