ክብሬን ገፍፎኛል፤ ዘውዴንም ከራሴ ላይ ወስዷል።
አማካሪዎችን ከጥበባቸው ያራቍታል፤ ፈራጆችንም ማስተዋል ይነሣል።
ካህናትን ከክህነታቸው ያዋርዳል፤ ለዘመናት የተደላደሉትንም ይገለብጣል።
“በቈዳዬ ላይ ማቅ ሰፍቻለሁ፤ ቀንዴን በዐፈር ውስጥ ቀብሬአለሁ።
“አሁን ግን በዕድሜ ከእኔ የሚያንሱ፣ ከመንጋዬ ጠባቂ ውሾች ጋራ እንዳይቀመጡ፣ አባቶቻቸውን የናቅኋቸው፣ እነዚህ ይሣለቁብኛል።
ከባሪያህ ጋራ የገባኸውን ኪዳን አፈረስህ፤ የክብር ዘውዱን ትቢያ ላይ ጥለህ አቃለልኸው።
ቅጥሩን ሁሉ አፈራረስህ፤ ምሽጉንም ደመሰስህ።
ግርማዊነቱን አጠፋህበት፤ ዙፋኑንም ከዐፈር ደባለቅኸው።
ሀብት ለዘላለም አይኖርምና፤ ዘውድም ከትውልድ ወደ ትውልድ ጸንቶ አይኖርም።
እናንተም የእግዚአብሔር ካህናት ተብላችሁ ትጠራላችሁ፤ የአምላካችን ባሮች ትባላላችሁ፤ የመንግሥታትን ሀብት ትመገባላችሁ፤ በብልጽግናቸውም ትኰራላችሁ።
አክሊላችን ከራሳችን ላይ ወድቋል፤ ወዮልን፤ ኀጢአት ሠርተናልና!
የኤፍሬም ክብር እንደ ወፍ በርሮ ይጠፋል፤ መውለድ፣ ማርገዝና መፀነስ የለም።