ቍጣ በሰይፍ መቀጣትን ያስከትላልና፣ ራሳችሁ ሰይፍን ፍሩ፤ በዚያ ጊዜ ፍርድ እንዳለ ታውቃላችሁ።”
ከጨለማ ወጥቶ ማምለጥ ይፈራል፤ ለሰይፍም የተመደበ ነው።
ናዕማታዊውም ሶፋር እንዲህ ሲል መለሰ፤
“እርሱ የሚገሥጽህ፣ ፍርድ ቤትም የሚያቀርብህ ስለምትፈራው ነውን?
ስለዚህ ክፉዎች በፍርድ ፊት፣ ኀጢአተኞችም በጻድቃን ማኅበር መቆም አይችሉም።
እግዚአብሔር ግን ለዘላለም በዙፋኑ ላይ ነው፤ መንበሩንም ለፍርድ አጽንቷል።
አንተ ወጣት በወጣትነትህ ጊዜ ደስ ይበልህ፤ በወጣትነትህም ዘመን ልብህ ደስ ያሰኝህ፤ የልብህን መንገድ፣ ዐይንህ የሚያየውንም ሁሉ ተከተል፤ ነገር ግን ስለ እነዚህ ነገሮች ሁሉ፣ አምላክ ወደ ፍርድ እንደሚያመጣህ ዕወቅ።
መልካምም ይሁን ክፉ፣ ስውር የሆነውን ነገር ሁሉ አንድ ሳይቀር፣ ማንኛውንም ሥራ አምላክ ወደ ፍርድ ያመጣዋልና።