የቤቴ እንግዶችና ሴት አገልጋዮቼ እንደ መጻተኛ ቈጠሩኝ፤ እንደ ባዕድም ተመለከቱኝ፤
ዘመዶቼ ትተውኛል፤ ወዳጆቼም ረስተውኛል።
አገልጋዬን ብጣራ፣ በአንደበቴም ብለምነው፣ አይመልስልኝም።
እግዚአብሔር ሆይ፤ ንቀት በዝቶብናልና፣ ማረን፤ እባክህ ማረን።