የድንኳኑ ብርሃን ይጨልማል፤ መብራቱም በላዩ ይጠፋል፤
ብርሃን በሌለበት ጨለማ በዳበሳ ይሄዳሉ፤ እንደ ሰካራምም ይንገዳገዳሉ።
ከእንግዲህ ባለጠጋ አይሆንም፤ ሀብቱም አይቈይም፤ ይዞታውም በምድር ላይ አይሰፋም።
ተማምኖ ከሚኖርበት ድንኳን ይነቀላል፤ ወደ ድንጋጤም ንጉሥ ይነዳል።
“የኀጢአተኞች መብራት የጠፋው ስንት ጊዜ ነው? የእግዚአብሔር ቍጣ መከራ የመጣባቸው፣ መቅሠፍትም የደረሰባቸው ስንት ጊዜ ነው?
ያን ጊዜ መብራቱ በራሴ ላይ ይበራ ነበር፤ በብርሃኑም በጨለማ ውስጥ ዐልፌ እሄድ ነበር፤
እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ መብራቴን ታበራለህ፤ አምላኬ፤ ጨለማዬን ያበራል።
ትዕቢተኛ ዐይን፣ እብሪተኛ ልብ፣ የክፉዎችም መብራት ኀጢአት ናቸው።
ግፈኛ ተስፋ የለውምና፤ የክፉዎችም መብራት ድርግም ብላ ትጠፋለች።
የክፉዎች መንገድ ግን እንደ ድቅድቅ ጨለማ ነው፤ ምን እንደሚያሰናክላቸውም አያውቁም።
አንተን በማጠፋ ጊዜ ሰማያትን እሸፍናለሁ፤ ከዋክብታቸውንም አጨልማለሁ፤ ፀሓይን በደመና እሸፍናለሁ፤ ጨረቃም ብርሃኗን አትሰጥም።
የመብራት ብርሃን፣ ዳግመኛ በአንቺ ውስጥ አይበራም፤ የሙሽራውና የሙሽራዪቱ ድምፅ፣ ዳግመኛ በአንቺ ውስጥ አይሰማም፤ ነጋዴዎችሽ የዓለም ታላላቅ ሰዎች ነበሩ፤ በአስማትሽም ሕዝቦች ሁሉ ስተዋል።