መታሰቢያው ከምድር ገጽ ይጠፋል፤ ስሙም በአገር አይነሣም።
ምሳሌዎቻችሁ የዐመድ ምሳሌዎች ናቸው፣ መከላከያችሁም የጭቃ ምሽግ ነው።
የተሸከመቻቸው ማሕፀን ትረሳቸዋለች፤ ትል ይቦጠቡጣቸዋል፤ ክፉዎች እንደ ዛፍ ይሰበራሉ፤ የሚያስታውሳቸውም የለም።
ዘሩ ተለይቶ ይጥፋ፤ ስማቸውም በሚቀጥለው ትውልድ ይደምሰስ።
መታሰቢያቸውን ከምድር ያጠፉ ዘንድ፣ ኀጢአታቸው ሁልጊዜ በእግዚአብሔር ፊት ይኑር።
የእግዚአብሔር ፊት ግን፣ መታሰቢያቸውን ከምድር ለማጥፋት በክፉ አድራጊዎች ላይ ነው።
ጠላቶቼ በክፋት በመናገር፣ “የሚሞተው መቼ ነው? ስሙስ የሚደመሰሰው ምን ቀን ነው?” ይላሉ።
“የእስራኤል ስም ከእንግዲህ እንዳይታወስ፣ ኑና ሕዝብ እንዳይሆኑ እንደምስሳቸው” አሉ።
ጠላቶች ለዘላለም ጠፉ፤ ከተሞቻቸውንም ገለባበጥሃቸው፤ መታሰቢያቸውም ተደምስሷል።
የጻድቃን መታሰቢያቸው በረከት ነው፤ የክፉዎች ስም ግን እንደ ጠፋ ይቀራል።
ክፉዎች ግን ከምድሪቱ ይወገዳሉ፤ ታማኝነት የጐደላቸውም ከርሷ ይነቀላሉ።
ከእነርሱ ጋራ በመቃብር አትሆንም፤ ምድርህን አጥፍተሃልና፤ ሕዝብህንም ፈጅተሃልና። የክፉ አድራጊዎች ዘር ፈጽሞ አይታወስም።
እነርሱ ሞተዋል፤ ከእንግዲህ በሕይወት አይኖሩም፤ መንፈሳቸው ተነሥቶ አይመጣም። አንተ ቀጣሃቸው፤ አጠፋሃቸው፤ መታሰቢያቸውንም ሁሉ ደመሰስህ።
አንቺ ነነዌ፤ እግዚአብሔር ስለ አንቺ እንዲህ ብሎ አዝዟል፤ “ስም የሚያስጠራ ትውልድ አይኖራችሁም፤ በአማልክታችሁ ቤት ያሉትን፣ የተቀረጹትን ምስሎችና ቀልጠው የተሠሩትን ጣዖታት እደመስሳለሁ፤ መቀበሪያህን እምስልሃለሁ፤ አንተ ክፉ ነህና።”