ዐይኔ ከሐዘን የተነሣ ፈዘዘ፤ መላ አካሌም እንደ ጥላ ሆነ።
ፊቴ ከልቅሶ የተነሣ ቀልቷል፤ ጨለማም በዐይኖቼ ቆብ ላይ ዐርፏል፤
ወዳጆቼ በንቀት ቢመለከቱኝም፣ ዐይኔ ወደ እግዚአብሔር ያነባል።
ጭምትርትር ያደረግኸኝ ምስክር ሆኖብኛል፣ ዐጥንቴን ያወጣው ክሳቴም ያጋልጠኛል።
አካሌ ቈስሎ ትልና ቅርፊት ለብሷል፤ ቈዳዬ አፈክፍኳል፤ ቍስሌም አመርቅዟል።
እንደ ምሽት ጥላ ከእይታ ተሰውሬአለሁ፤ እንደ አንበጣም ረግፌአለሁ።
ዐይኖቼ በሐዘን ብዛት ደክመዋል፤ ከጠላቶቼም ሁሉ የተነሣ ማየት ተስኗቸዋል።
እናንተ ክፉ አድራጊዎች ሁሉ፤ ከእኔ ራቁ፤ እግዚአብሔር የልቅሶዬን ድምፅ ሰምቷልና።
ሰው በሕይወት ሳለ፣ እንደ ጥላ በሚያልፉት ጥቂትና ከንቱ በሆኑት ቀኖቹ፣ ለሰው መልካም የሆነውን የሚያውቅ ማን ነው? እርሱ ከሄደ በኋላስ ከፀሓይ በታች የሚሆነውን ማን ሊነግረው ይችላል?
ከዚህ የተነሣ ልባችን ደከመ፤ ከእነዚህ የተነሣም ዐይናችን ፈዘዘ፤