“ነገር ግን እናንተ ሁላችሁ፣ እስኪ ተመልሳችሁ እንደ ገና ሞክሩ! ከመካከላችሁ አንድም ጠቢብ አላገኝም።
“በርግጥ ሰው ማለት እናንተ ናችኋ! ጥበብም ከእናንተ ጋራ ትሞታለቻ!
እኛ የማናውቀው አንተ ግን የምታውቀው ምን ነገር አለ? እኛስ የሌለን አንተ ያለህ ማስተዋል የቱ ነው?
ዕድሜዬ ዐለቀ፤ ዕቅዴም ከሸፈ፤ የልቤም ሐሳብ ከንቱ ሆነ።
እንዳያስተውሉ ልባቸውን ይዘሃል፤ ስለዚህ ድል አትሰጣቸውም።
ለምን እንደ ከብት መንጋ እንቈጠራለን? እንደ ደንቈሮስ ለምን ታየናለህ?
ጠቢባን የሚሆኑት በዕድሜ የገፉ ብቻ አይደሉም፤ የሚያስተውሉም ሽማግሌዎች ብቻ አይደሉም።
እግዚአብሔር ይህን ለኢዮብ ከተናገረ በኋላ፣ ቴማናዊውን ኤልፋዝን እንዲህ አለው፤ “እንደ አገልጋዬ እንደ ኢዮብ ስለ እኔ ቅን ነገር ስላልተናገራችሁ፣ ቍጣዬ በአንተና በሁለቱ ባልንጀሮችህ ላይ ነድዷል።
መለስ በሉ፤ ፍርደ ገምድል አትሁኑ፤ ጽድቄ ጸንታ ቆማለችና መለስ ብላችሁ አስተውሉ።
በዚያ ጊዜም እንደ ገና በጻድቁና በኀጢአተኛው መካከል፣ እግዚአብሔርን በሚያገለግለውና በማያገለግለው መካከል ያለውን ልዩነት ታያላችሁ።
ጠቢብ የት አለ? ሊቅስ የት አለ? የዘመኑስ ፈላስፋ የት አለ? እግዚአብሔር የዓለምን ጥበብ ሞኝነት አላደረገምን?
ይህንም የምለው ላሳፍራችሁ ብዬ ነው። ለመሆኑ በወንድሞች መካከል ለመፍረድ የሚበቃ ጠቢብ ሰው በመካከላችሁ የለምን?