እኛ የማናውቀው አንተ ግን የምታውቀው ምን ነገር አለ? እኛስ የሌለን አንተ ያለህ ማስተዋል የቱ ነው?
ነገር ግን እኔም እንደ እናንተ አእምሮ አለኝ፤ ከእናንተ አላንስም፤ እንዲህ ያለውን ነገር የማያውቅ ማን ነው?
እናንተ የምታውቁትን፣ እኔም ዐውቃለሁ፤ ከእናንተ የማንስ አይደለሁም።
ቃሉን ለማየትና ለመስማት፣ እነማን የእግዚአብሔር ምክር ባለበት ቆመዋል? ቃሉን ያደመጠ፣ የሰማስ ማን ነው?
እናንተ የምትመለከቱት ውጫዊውን ነገር ብቻ ነው። ማንም የክርስቶስ በመሆኑ ቢመካ እርሱ የክርስቶስ እንደ ሆነ ሁሉ እኛም የክርስቶስ መሆናችንን ሊገነዘብ ይገባዋል።
እኔ ግን “ታላላቅ ሐዋርያት” ከሚባሉት በምንም የማንስ አይመስለኝም።