ከጨለማ አያመልጥም፤ ቅርንጫፎቹን ነበልባል ያደርቃቸዋል፤ በእግዚአብሔርም እስትንፋስ ይወሰዳል።
ከጨለማ ወጥቶ ማምለጥ ይፈራል፤ ለሰይፍም የተመደበ ነው።
የአሞራ እራት ለመሆን ይቅበዘበዛል፤ የጨለማ ቀን መቅረቡን ያውቃል።
የዐመፀኞች ጉባኤ ትመክናለች፤ የጉቦ ሱሰኞችም ድንኳን በእሳት ትበላለች።
ሥሩ ከታች ይደርቃል፤ ቅርንጫፉም ከላይ ይረግፋል።
ከብርሃን ወደ ጨለማ ይጣላል፤ ከዓለምም ይወገዳል።
ሀብቱ ለድቅድቅ ጨለማ ተዳርጓል፤ ሰው ባላራገበው እሳት ይበላል፤ በድንኳኑም ውስጥ የተረፈውን ይልሳል።
‘በርግጥ ጠላቶቻችን ጠፍተዋል፤ ሀብታቸውም በእሳት ተበልቷል።’
ይህ የሚያቃጥልና የሚያጠፋ እሳት ነው፤ ቡቃያዬንም ባወደመ ነበር።
በእግዚአብሔር እስትንፋስ ይጠፋሉ፤ በቍጣውም ወላፈን ይደመሰሳሉ።
ቀኑ ጨለማ ይሆንባቸዋል፤ በቀትርም ጊዜ በሌሊት እንዳለ ሰው በዳበሳ ይሄዳሉ።
ነገር ግን ለድኾች በጽድቅ ይፈርዳል፤ ለምድር ምስኪኖችም ፍትሕን ይበይናል፤ በአፉ በትር ምድርን ይመታል፤ በከንፈሩም እስትንፋስ ክፉዎችን ይገድላል።
ከቀድሞ ጀምሮ ቶፌት የተባለ የማቃጠያ ስፍራ ተዘጋጅቷል፤ ለንጉሡም ተበጅቷል፤ ማንደጃ ጕድጓዱም ሰፊና ጥልቅ ነው፤ በውስጡም ብዙ እሳትና ማገዶ አለ፤ የእግዚአብሔርም እስትንፋስ እንደ ፈሳሽ ድኝ ያቀጣጥለዋል።
ስለዚህ በነቢያቴ ቈራረጥኋችሁ፤ በአፌም ቃል ገደልኋችሁ፣ ፍርዴም እንደ መብረቅ በላያችሁ አበራ።
“ንጉሡም አገልጋዮቹን፣ ‘እጅና እግሩን አስራችሁ በውጭ ወዳለው ጨለማ አውጥታችሁ ጣሉት፤ በዚያ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል’ አላቸው፤
“ከዚያም በግራው በኩል ላሉት ደግሞ እንዲህ ይላቸዋል፤ ‘እናንተ የተረገማችሁ፤ ለዲያብሎስና ለመላእክቱ ወደ ተዘጋጀው የዘላለም እሳት ከእኔ ተለይታችሁ ሂዱ፤
መንግሥተ ሰማይ ተዘጋጅቶላቸው የነበሩት ግን ወደ ውጭ ወደ ጨለማው ይጣላሉ። በዚያም ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል።”
እነዚህ ሰዎች የደረቁ ምንጮችና በዐውሎ ነፋስ የሚነዱ ደመናዎች ናቸው፤ የሚጠብቃቸውም ድቅድቅ ጨለማ ነው፤
የነውራቸውን ዐረፋ የሚደፍቁ የተቈጡ የባሕር ማዕበል፣ ድቅድቅ ጨለማ ለዘላለም የሚጠብቃቸው ተንከራታች ከዋክብት ናቸው።
ሕዝቦችን የሚመታበት ስለታም ሰይፍ ከአፉ ወጣ፤ “በብረት በትርም ይገዛቸዋል።” እርሱም ሁሉን ቻይ የሆነውን የእግዚአብሔርን የብርቱ ቍጣ ወይን መጭመቂያ ይረግጣል።