ክፉ ሰው ዕድሜውን ሙሉ፣ ጨካኙም በተመደበለት ዘመን ሁሉ ይሠቃያል።
እነሆ፤ ዛሬ ከምድሪቱ አባረርኸኝ፤ ከፊትህም እሸሸጋለሁ፤ በምድር ላይ ኰብላይና ተንከራታች እሆናለሁ፤ የሚያገኘኝም ሁሉ ይገድለኛል።”
ምድሪቱ ለአባቶቻቸው ተሰጠች፤ በመካከላቸውም ባዕድ አልተቀመጠም፤
ጭንቀትና ሐዘን ያስፈራሩታል፤ ለማጥቃት እንደ ተዘጋጀ ንጉሥም ያይሉበታል፤
“ሁሉን ቻይ አምላክ ለምን የፍርድ ቀን አይወስንም? እርሱን የሚያውቁትስ ለምን ያን ቀን እንዲያው ይጠባበቃሉ?
“እግዚአብሔር ለክፉው ሰው የመደበው ዕድል ፈንታ፣ ግፈኛም ሁሉን ቻይ አምላክ የሚቀበለው ቅርስ ይህ ነው፦
ጥበብን የተሞላ ልብ ይኖረን ዘንድ፣ ዕድሜያችንን መቍጠር አስተምረን።
ከፀሓይ በታች በሁሉም ላይ የሚሆነው ክፋት ይህ ነው፤ የሁሉም የመጨረሻ ዕጣ ፈንታ አንድ ነው። በዚህም ላይ የሰዎች ልብ በክፋት የተሞላ ነው፤ በሕይወት እያሉም በልባቸው ውስጥ እብደት አለ፤ በመጨረሻም ወደ ሙታን ይወርዳሉ።
እስከ አሁን ድረስ ፍጥረት ሁሉ በምጥ ጊዜ እንዳለው ሥቃይ በመቃተት ላይ እንደሚገኝ እናውቃለን።