“አድምጠኝ፤ በግልጽ አስረዳሃለሁ፤ ያየሁትንም እነግርሃለሁ፤
“ይህን ሁሉ ዐይኔ አይቷል፤ ጆሮዬም ሰምቶ አስተውያለሁ፤
ታዲያ፣ ክፋትን እንደ ውሃ የሚጠጣ፣ አስጸያፊና ርኩስ ሰውማ እንዴት ይታመን!
ጠቢባን ከአባቶቻቸው የተቀበሉትን፤ ሳይሸሽጉ የተናገሩትን አስረዳሃለሁ፤
“አሁን ግን ኢዮብ ሆይ፣ ንግግሬን ስማ፤ የምለውንም ሁሉ አድምጥ።
“እናንተ ጠቢባን፣ ቃሌን ስሙ፤ ዐዋቂዎችም አድምጡኝ።
“በእግዚአብሔር ፈንታ ሆኜ የምለው አለኝ፤ ጥቂት ታገሠኝና እነግርሃለሁ።
“እነሆ፤ ይህን ሁሉ መርምረናል፤ እውነት ሆኖ አግኝተነዋል፤ ስለዚህ ልብ በል፤ ተቀበለውም።”