ምላስ የምግብን ጣዕም እንደሚለይ፣ ጆሮ ቃላትን አይለይምን?
ምላስ ምግብን አጣጥሞ እንደሚለይ፣ ጆሮም የንግግርን ለዛ ለይቶ ያውቃል።
ክፋት በአንደበቴ አለን? አፌስ ተንኰልን መለየት አይችልምን?
ይህን የምናገረው አስተዋይ ለሆኑ ሰዎች ነው፤ ስለምናገረው ነገር እናንተው ፍረዱ።
ይኸውም ከሁሉ የሚሻለውን ለይታችሁ እንድታውቁ፣ እስከ ክርስቶስም ቀን ድረስ ንጹሓንና ነቀፋ የሌለባችሁ እንድትሆኑ፣
ጠንካራ ምግብ ግን መልካሙን ከክፉው ለመለየት ራሳቸውን ላስለመዱ፣ ለበሰሉ ሰዎች ነው።
ጌታ መልካም መሆኑን ቀምሳችኋልና።