“ይህ ሁሉ ቃል መልስ ማግኘት አይገባውምን? ወይስ ተናጋሪ ሰው እንደ እውነተኛ ይቈጠርን?
ነዕማታዊው ሶፋር እንዲህ ሲል መለሰ፤
“ጠቢብ ሰው በከንቱ ንግግር መልስ ይሰጣልን? ወይስ በምሥራቅ ነፋስ ሆዱን ይሞላል?
ይህ ከንቱ ንግግር አያልቅምን? ትለፈልፍ ዘንድ የሚገፋፋህ ምንድን ነው?
“ይህን ንግግር የምትጨርሰው መቼ ነው? እስኪ ልብ ግዛ፤ ከዚያ በኋላ እንነጋገራለን።
“እንዲህ ያለውን ነገር የምትናገረው፣ ቃልህም እንደ ብርቱ ነፋስ የሚሆነው እስከ መቼ ነው?
ምላሰኛ በምድሪቱ ጸንቶ አይኑር፤ ዐመፀኛውን ሰው ክፋት አሳድዶ ያጥፋው።
ከቃላት ብዛት ኀጢአት አይታጣም፤ አንደበቱን የሚገታ ግን ጠቢብ ነው።
ወደ እግዚአብሔር ቤት ስትሄድ እግርህን ጠብቅ። ለመስማት መቅረብ የሞኞችን መሥዋዕት ከማቅረብ ይበልጣል፤ እነርሱ ክፉ እንደሚሠሩ አያውቁምና።
በሥራ ብዛት ሕልም እንደሚታይ፣ ብዙ ቃል ባለበትም የሞኝ ንግግር ይገለጣል።
ከኤፊቆሮስና ከኢስጦኢክ የፍልስፍና ወገን የሆኑትም ወደ እርሱ መጥተው ይከራከሩት ነበር። አንዳንዶቹ፣ “ይህ ለፍላፊ ምን ለማለት ይፈልጋል?” ይሉ ነበር፤ ሌሎች ደግሞ ስለ ኢየሱስና ስለ ትንሣኤው የምሥራች ሲሰብክ ሰምተው፣ “ስለ አዳዲስ ባዕዳን አማልክት የሚናገር ይመስላል” አሉ።
የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፤ ይህን አስተውሉ፤ ሰው ሁሉ ለመስማት የፈጠነ፣ ለመናገር የዘገየ፣ ለቍጣም የዘገየ ይሁን፤