ሕይወትህ ከቀትር ይልቅ ያበራል፤ ጨለማውም እንደ ንጋት ይሆናል።
ዳዊትም በመላው ጉባኤ ፊት እግዚአብሔርን እንዲህ ሲል አመሰገነ፤ “የአባታችን የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤ ከዘላለም እስከ ዘላለም ለአንተ ምስጋና ይሁን።
ተስፋ ስላለ ተደላድለህ ትቀመጣለህ፤ ዙሪያህን ትመለከታለህ፣ ያለ ሥጋት ታርፋለህ።
በዚያ ጊዜ በሁሉን ቻይ አምላክ ደስ ይልሃል፤ ፊትህንም ወደ እግዚአብሔር ታቀናለህ።
ያሰብኸው ይከናወንልሃል፤ በመንገድህም ላይ ብርሃን ይበራል።
ያን ጊዜ መብራቱ በራሴ ላይ ይበራ ነበር፤ በብርሃኑም በጨለማ ውስጥ ዐልፌ እሄድ ነበር፤
ቸር፣ ርኅሩኅና ጻድቅ እንደ መሆኑ፣ ለቅን ሰው በጨለማ ውስጥ ብርሃን ይወጣለታል።
ጽድቅህን እንደ ብርሃን፣ ፍትሕህን እንደ ቀትር ፀሓይ ያበራዋል።
ባረጁ ጊዜ እንኳ ያፈራሉ፤ እንደ ለመለሙና እንደ ጠነከሩም ይኖራሉ።
ብርሃን ለጻድቃን፣ ሐሤትም ልባቸው ለቀና ወጣ።
የጻድቃን መንገድ ሙሉ ቀን እስኪሆን ድረስ፣ ብርሃኑ እየጐላ እንደሚሄድ የማለዳ ውጋጋን ነው።
እግዚአብሔርን እንወቀው፤ የበለጠ እናውቀውም ዘንድ አጥብቀን እንከተለው፤ እንደ ንጋት ብርሃን፣ በርግጥ ይገለጣል፤ ምድርን እንደሚያረሰርስ የበልግ ዝናብ፣ እንደ ክረምትም ዝናብ ወደ እኛ ይመጣል።”
ስሜን ለምትፈሩ ለእናንተ ግን የጽድቅ ፀሓይ በክንፎቿ ፈውስ ይዛ ትወጣለች፤ እናንተም እንደ ሠባ እንቦሳ እየቦረቃችሁ ትወጣላችሁ።