ሰላምን ተስፋ አደረግን፤ መልካም ነገር ግን አልመጣም፤ የፈውስ ጊዜን ተመኘን፤ ነገር ግን ሽብር ብቻ ሆነብን።
ነገር ግን መልካም ስጠብቅ፣ ክፉ ነገር ደረሰብኝ፤ ብርሃንንም ስጠባበቅ፣ ጨለማ መጣብኝ።
በምድረ በዳ ባሉት ወና ኰረብቶች ላይ፣ አጥፊዎች ይሰማራሉ፤ የእግዚአብሔር ሰይፍ ከምድር ጫፍ እስከ ምድር ጫፍ፣ አንዳች ሳያስቀር ይበላል፤ የሚተርፍም የለም።
ይሁዳን ፈጽመህ ጥለኸዋልን? ነፍስህስ ጽዮንን ተጸየፈቻትን? ፈውስ እስከማይገኝልን ድረስ፣ ለምን ክፉኛ መታኸን? ሰላምን ተስፋ አደረግን፤ ሆኖም በጎ ነገር አላገኘንም፤ የፈውስን ጊዜ ተጠባበቅን፤ ነገር ግን ሽብር ብቻ ሆነ።
እኔም፣ “ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ ሰይፍ ዐንገታቸው ላይ ተቃጥቶ ሳለ፣ ‘ሰላም ይሆንላችኋል’ ብለህ ይህን ሕዝብና ኢየሩሳሌምን ለምን እጅግ አታለልህ?” አልሁ።
ጠላት ሰይፍ ታጥቋል፤ በየቦታውም ሽብር ሞልቷል፤ ስለዚህ ወደ ውጭ አትውጡ፤ በየመንገዱ አትዘዋወሩ።
የሕዝቤን ቍስል ብርቱ እንዳይደለ በመቍጠር፣ የተሟላ ፈውስ ሳይኖር እንዲሁ ያክማሉ፤ ሰላም ሳይኖር፣ “ሰላም፣ ሰላም” ይላሉ።
ሽብር በመጣ ጊዜ ሰላምን ይሻሉ፤ ነገር ግን አያገኟትም።
ከመከራው መገላገልን በመሻት፣ በማሮት የሚኖሩ በሥቃይ ይወራጫሉ፤ እስከ ኢየሩሳሌም በር ሳይቀር፣ ክፉ ነገር ከእግዚአብሔር ዘንድ መጥቷልና።
ሰዎች፣ “ሰላምና ደኅንነት ነው” ሲሉ፣ ምጥ እርጉዝ ሴትን እንደሚይዛት እንዲሁ ጥፋት በድንገት ይመጣባቸዋል፤ ከቶም አያመልጡም።