Biblia Todo Logo
ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች
- ማስታወቂያዎች -



ኤርምያስ 8:13

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

“ ‘ያመረቱትን ሁሉ እወስድባቸዋለሁ፤ ይላል እግዚአብሔር፤ በወይን ተክል ላይ የወይን ፍሬ አይኖርም፤ በበለስ ዛፍ ላይ የበለስ ፍሬ አይገኝም፤ ቅጠሎቻቸውም ይረግፋሉ። የሰጠኋቸው በሙሉ፣ ከእነርሱ ይወሰድባቸዋል።’ ”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

25 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከሩብ ጋሻ የወይን ቦታ አንድ የባዶስ መስፈሪያ ያህል የወይን ጭማቂ ብቻ ይገኛል፤ አንድ የቆሮስ መስፈሪያ ዘር ተዘርቶ አንድ የኢፍ መስፈሪያ እህል ብቻ ይሰጣል።”

ቢጾሙም ጩኸታቸውን አልሰማም፤ የሚቃጠል መሥዋዕትና የእህል ቍርባን ቢያቀርቡም አልቀበላቸውም፤ ነገር ግን በሰይፍ፣ በራብና በቸነፈር አጠፋቸዋለሁ።”

ስለዚህ በስሜ የሐሰት ትንቢት ስለሚናገሩ ነቢያት እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ እኔ ሳልልካቸው፣ ‘ሰይፍና ራብ በዚች ምድር ላይ አይመጣም’ የሚሉ እነዚህ ነቢያት በሰይፍና በራብ ይጠፋሉ፤

በውሃ ዳር እንደ ተተከለ፣ ሥሩንም ወደ ወንዝ እንደ ሰደደ ዛፍ ነው፣ ሙቀት ሲመጣ አይፈራም፤ ቅጠሉም ዘወትር እንደ ለመለመ ነው፤ በድርቅ ዘመን አይሠጋም፤ ፍሬ ማፍራቱንም አያቋርጥም።”

ሰብልህንና ምግብህን ጠራርገው ይበሉብሃል፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆችህን ይውጣሉ፤ በጎችህንና ከብቶችህን ይፈጃሉ፤ የወይን ተክሎችህንና የበለስ ዛፎችህን ያወድማሉ፤ የታመንህባቸውንም የተመሸጉ ከተሞች በሰይፍ ያጠፏቸዋል።

“ ‘ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ቍጣዬና መዓቴ በዚህ ስፍራ በሰውና በእንስሳ ላይ፣ በዱር ዛፍና በምድር ፍሬ ላይ ይፈስሳል፤ ይነድዳል፤ አይጠፋምም።

ስለዚህ መዓቴን አፈስስባቸዋለሁ፤ በጽኑ ቍጣዬም አነድዳቸዋለሁ፤ ያደረጉትንም በራሳቸው ላይ እመልሳለሁ፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።”

ከውሽሞቼ የተቀበልሁት ዋጋ ነው የምትለውን የወይን ተክሎቿንና የበለስ ዛፎቿን አጠፋለሁ፤ ጫካ አደርገዋለሁ፤ የዱር አራዊትም ይበሉታል።

የወይን ቦታዬን ባድማ አደረገው፤ የበለስ ዛፎቼንም ቈራረጠ፤ ቅርንጫፎቻቸው ነጭ ሆነው እስኪታዩ ድረስ፣ ቅርፊታቸውን ልጦ፣ ወዲያ ጣላቸው።

ኀይላችሁ በከንቱ ያልቃል፤ ምድራችሁ እህሏን፣ የምድሪቱ ዛፎችም ፍሬዎቻቸውን አይሰጡምና።

ምንም እንኳ የበለስ ዛፍ ባያፈራ፣ ከወይን ተክልም ፍሬ ባይገኝ፣ የወይራም ዛፍ ፍሬ ባይሰጥ፣ ዕርሻዎችም ሰብል ባይሰጡ፣ የበጎች ጕረኖ እንኳ ባዶውን ቢቀር፣ ላሞችም በበረት ውስጥ ባይገኙ፣

እኔም በዕርሻዎችና በተራሮች፣ በእህሉና በአዲሱ ወይን ጠጅ፣ በዘይቱና ምድር በምታፈራው ሁሉ፣ በሰውና በእንስሳ፣ በእጆቻችሁም ሥራ ላይ ድርቅ አመጣሁ።”

የእጃችሁን ሥራ ሁሉ በዋግ፣ በአረማሞና በበረዶ መታሁት፤ እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም’ ይላል እግዚአብሔር፤

ስለ እናንተ ተባዩን እገሥጻለሁ፤ አዝመራችሁን አይበላም፤ ዕርሻ ላይ ያለ የወይን ተክላችሁም ፍሬ አልባ አይሆንም” ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር።

በመንገድ ዳርም አንድ የበለስ ዛፍ አይቶ ወደ እርሷ ሲሄድ ከቅጠል በቀር ምንም ስላላገኘባት፣ “ከአሁን ጀምሮ ለዘላለም ፍሬ አይኑርብሽ!” አላት፤ የበለሷም ዛፍ ወዲያውኑ ደረቀች።

ፀሓይ በነዲድ ሙቀቷ ወጥታ ሣሩን ታጠወልጋለችና፤ አበባው ይረግፋል፤ ውበቱም ይጠፋል፤ እንዲሁም ባለጠጋ ሰው፣ በዕለት ተግባሩ ሲዋትት ሳለ ይጠፋል።




ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች