መንገዳችሁንና ሥራችሁን በርግጥ ብታሳምሩ፣ በመካከላችሁ ቅንነት ቢኖር፣
ዕሺ ብትሉ፣ ብትታዘዙም የምድርን በረከት ትበላላችሁ፤
“ምክር ለግሱን፤ ውሳኔ ስጡን፤ በቀትር ጥላችሁን እንደ ሌሊት አጥሉብን፤ የሸሹትን ደብቁ፤ ስደተኞችን አሳልፋችሁ አትስጡ።
የዳዊት ቤት ሆይ፤ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ ‘ካደረጋችሁት ክፋት የተነሣ፣ ቍጣዬ እንዳይቀጣጠል፣ ማንም ሊያጠፋው እስከማይችል እንዳይነድድ፣ በየማለዳው ፍትሕን አድርጉ፤ የተበዘበዘውን ሰው፣ ከጨቋኙ እጅ አድኑት።
“በዝግባ ዕንጨት ብዛት፣ የነገሥህ ይመስልሃልን? አባትህስ ፍትሕንና ጽድቅን በማድረጉ፣ የሚበላውና የሚጠጣው ጐድሎት ነበርን? እነሆ፤ ሁሉም መልካም ሆነለት።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ፍትሕንና ጽድቅን አድርጉ፤ የተበዘበዘውን ከጨቋኙ እጅ አድኑት፤ መጻተኛውን፣ ወላጅ የሌለውንና መበለቲቱን አትበድሉ፤ አትግፏቸውም፤ በዚህም ስፍራ ንጹሕ ደም አታፍስሱ።
አሁንም መንገዳችሁንና ሥራችሁን አስተካክሉ፣ አምላካችሁን እግዚአብሔርን ታዘዙ። እግዚአብሔርም በእናንተ ላይ ለማምጣት የተናገረውን ክፉ ነገር ይተዋል።
የእስራኤል አምላክ፣ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ መንገዳችሁንና ሥራችሁን አስተካክሉ፤ እኔም በዚህ ስፍራ እንድትኖሩ አደርጋችኋለሁ።
እጁን ደኻን ከመበደል ቢሰበስብ፣ ዐራጣ ወይም ከፍተኛ ወለድ ባይቀበል፣ ሕጌን ቢጠብቅ፣ ሥርዐቴንም ቢከተል፣ በሕይወት ይኖራል እንጂ በአባቱ ኀጢአት አይሞትም።
“በቅንነትና በትክክል የሚሠራ፣ ጻድቅ ሰው ቢገኝ፣
በዐራጣ አያበድርም፣ ከፍተኛ ወለድም አይቀበልም። እጁን ከበደል ይሰበስባል፤ በሰውና በሰው መካከል በትክክል ይፈርዳል።
አንዱ ሌላውን አያታልል፤ አምላክህን ፍራ፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ።
ኢየሩሳሌምና በዙሪያዋ ያሉ ከተሞች በሰላምና በብልጽግና ላይ ሳሉ፣ የደቡብና የምዕራብ ኰረብቶች ግርጌ የሰው መኖሪያም በነበሩበት ጊዜ፣ እግዚአብሔር በቀደሙት ነቢያት የተናገረው ቃል ይህ አልነበረምን?’ ”
በኢያቢስ ገለዓድ ከሚኖረው ሕዝብ መካከል ወንድ ያልደረሰባቸው አራት መቶ ደናግል አገኙ፤ በከነዓን ምድር በሴሎ ወደሚገኘውም ሰፈር አመጧቸው።
በዚያ ዕለት ዲቦራና የአቢኒኤም ልጅ ባርቅ ይህን ቅኔ ተቀኙ፤