እረኞች መንጎቻቸውን ይዘው ይመጡባታል፤ ድንኳናቸውን በዙሪያዋ ይተክላሉ፤ እያንዳንዳቸውም በየአቅጣጫቸው መንጋቸውን ያሰማራሉ።
እግዚአብሔርም በኢዮአቄም ላይ ባቢሎናውያን፣ ሶርያውያን፣ ሞዓባውያንና አሞናውያን አደጋ ጣዮችን ላከበት፤ በአገልጋዮቹ በነቢያቱ አማካይነት በተነገረው በእግዚአብሔር ቃል መሠረት ይሁዳን ያጠፉ ዘንድ እነዚህን ላከ።
ብዙ እረኞች የወይን ቦታዬን ያጠፋሉ፤ ይዞታዬንም ይረግጣሉ፤ ደስ የምሰኝበትንም ማሳ፣ ጭር ያለ በረሓ ያደርጉታል።
የአሦር ንጉሥ ሆይ፤ እረኞችህ አንቀላፉ፤ መኳንንትህ ዐርፈው ተኙ፤ ሕዝብህ ሰብሳቢ ዐጥተው፣ በተራራ ላይ ተበትነዋል።
ጠላቶችሽ ዙሪያሽን ቅጥር ሠርተው፣ ከየአቅጣጫውም ከብበው አንቺን የሚያስጨንቁበት ጊዜ ይመጣልና፤