ቀስትና ጦር ይዘዋል፤ ጨካኞችና ምሕረት የለሽ ናቸው፤ ፈረሶቻቸውን ሲጋልቡ፣ ድምፃቸው እንደ ተናወጠ ባሕር ነው፤ የጽዮን ልጅ ሆይ፤ ለሰልፍ የታጠቁ ሆነው፣ ሊወጉሽ ይመጣሉ።”
በዚህ ቀን ኖብ ይደርሳሉ፤ እጃቸውን በኢየሩሳሌም ኰረብታ፣ በጽዮን ሴት ልጅ ተራራ ላይ በዛቻ ነቀነቁ።
ቀስታቸው ጐበዞችን ይፈጃል፤ ሕፃናትን አይምሩም፤ ዐይናቸውም ለልጆች አይራራም።
ወዮ! የብዙ ሕዝቦች የቍጣ ድምፅ እንደ ባሕር ሞገድ ይጮኻል! አቤት፤ የሰዎች ከፍተኛ ጩኸት እንደ ኀይለኛ ውሃ ያስገመግማል!
ግብጻውያንን አሳልፌ ለጨካኝ ጌታ ክንድ እሰጣቸዋለሁ፤ አስፈሪ ንጉሥም ይገዛቸዋል” ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “እነሆ፤ ጥፋት፣ ከአገር ወደ አገር እየተዛመተ መጥቷል፤ ብርቱ ዐውሎ ነፋስ፣ ከምድር ዳርቻ ተነሥቷል።”
የሰሜንን ሕዝብ ሁሉ፣ አገልጋዬንም የባቢሎንን ንጉሥ ናቡከደነፆርን እጠራለሁ” ይላል እግዚአብሔር፤ “በዚህች ምድርና በነዋሪዎቿም ላይ፣ በአካባቢዋም ባሉ ሕዝቦች ሁሉ ላይ አመጣባቸዋለሁ፤ ፈጽሜም አጠፋቸዋለሁ፤ ሰዎች የሚጸየፏቸውና የሚሣለቁባቸው፣ የዘላለምም ባድማ አደርጋቸዋለሁ፤
ወዳጆችህ ሁሉ ረስተውሃል፤ ስለ አንተም ግድ የላቸውም። ጠላት እንደሚመታ መታሁህ፤ እንደ ጨካኝም ቀጣሁህ፤ በደልህ ታላቅ፣ ኀጢአትህም ብዙ ነውና።
እነሆ፤ እንደ ደመና ይንሰራፋል፤ ሠረገሎቹ እንደ ዐውሎ ነፋስ ይመጣሉ፤ ፈረሶቹም ከንስር ይፈጥናሉ፤ መጥፋታችን ነውና ወዮልን!
“ይህን ለሕዝቦች አሳውቁ፤ ለኢየሩሳሌምም እንዲህ ብላችሁ በይፋ ንገሩ፤ ‘ከብበው የሚያስጨንቁ ከሩቅ አገር ይመጣሉ፤ በይሁዳ ከተሞችም ላይ ይደነፋሉ፤
ከፈረሰኞችና ከቀስተኞች ጩኸት የተነሣ፣ ከተማ ሁሉ ይሸሻል፤ አንዳንዶች ደን ውስጥ ይገባሉ፤ ሌሎችም ቋጥኝ ላይ ይወጣሉ፤ ከተሞች ሁሉ ባዶ ቀርተዋል፤ የሚኖርባቸውም የለም።
የፍላጻቸው ሰገባ እንደ ተከፈተ መቃብር ነው፤ ሁሉም ብርቱ ተዋጊዎች ናቸው።
“እነሆ፤ ሰራዊት ከሰሜን ይመጣል፤ አንድ ኀያል መንግሥትና ብዙ ነገሥታት፣ ከምድር ዳርቻ ተነሣሥተዋል።
ቀስትና ጦር ይዘዋል፤ ጨካኞች ናቸው፤ ምሕረትም አያደርጉም፤ በፈረሳቸው እየጋለቡ ሲመጡ፣ ድምፃቸው እንደ ባሕር ሞገድ ይተምማል፤ ያስገመግማል። አንቺ የባቢሎን ሴት ልጅ ሆይ፤ ለጦርነት እንደ ተዘጋጁ ተዋጊዎች ይመጡብሻል።
“በርሷ ላይ ጦርነት ዐውጁ፤ ተነሡ በቀትር አደጋ እንጣልባት፤ ወዮ! ቀኑ እኮ መሸብን! ጥላው ረዘመ።
የጠላት ፈረሶች ፉርፉርታ፣ ከዳን ይሰማል፤ በድንጉላ ፈረሶቻቸው ማሽካካት፣ መላዋ ምድር ተንቀጠቀጠች። ምድሪቱንና በውስጧ ያለውን ሁሉ፣ ከተማዪቱንና በውስጧ የሚኖሩትን ሁሉ፣ ሊውጡ መጡ።
መዓቴን በላይህ አፈስሳለሁ፤ የቍጣዬንም እሳት አነድድብሃለሁ፣ በጥፋት ለተካኑ፣ ለጨካኞች ሰዎች አሳልፌ እሰጥሃለሁ።
እግዚአብሔር እንደ ንስር ፈጥኖ የሚወርድንና ቋንቋውን የማታውቀውን ሕዝብ እጅግ ሩቅ ከሆነ፣ ከምድርም ዳርቻ ያስነሣብሃል፤