ሕዝቦቿ ሁሉ እንደ ደቦል አንበሳ ያገሣሉ፤ እንደ አንበሳ ግልገልም ያጕረመርማሉ።
አባትህና ሰዎቹ የማይበገሩ ተዋጊዎችና ግልገሎቿ እንደ ተነጠቁባት የዱር ድብ አስፈሪ መሆናቸውን አንተም ታውቃለህ፤ በተጨማሪም አባትህ በቂ ልምድ ያለው ነው፤ ሌሊቱን ከሰራዊቱ ጋራ አያድርም፤
አንበሶች ሊያጡ፣ ሊራቡም ይችላሉ፤ እግዚአብሔርን የሚሹ ግን መልካም ነገር አይጐድልባቸውም።
አምላክ ሆይ፤ ጥርሳቸውን በአፋቸው ውስጥ ስበር፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ የአንበሶቹን መንጋጋ አወላልቅ!
አንበሳ አይኖርበትም፤ ነጣቂ አውሬም አይወጣበትም፤ እነዚህማ በዚያ ስፍራ አይገኙም፤ የዳኑት ብቻ በዚያ ይሄዳሉ፤
ጩኸታቸው እንደ አንበሳ ነው፤ እንደ አንበሳ ደቦል ያገሣሉ፤ ያደኑትንም ይዘው ይጮኻሉ፤ ተሸክመውት ይሄዳሉ፤ የሚያስጥልም የለም።
አንበሶች በርሱ ላይ አገሡ፤ በኀይለኛ ድምፅም ጮኹበት። ምድሩን ባድማ አድርገውበታል፤ ከተሞቹ ተቃጥለዋል፤ ወናም ሆነዋል።
የእረኞችን ዋይታ ስሙ፤ ክብራቸው ተገፍፏልና፤ የአንበሶችን ጩኸት ስሙ፤ ጥቅጥቅ ያለው የዮርዳኖስ ደን ወድሟል!
እርሷም፣ “ሳምሶን፤ ፍልስጥኤማውያን መጡብህ!” አለችው። ሳምሶን ከእንቅልፉ ነቅቶ፣ “እንደ ወትሮው አደርጋለሁ” አለ፤ ነገር ግን እግዚአብሔር እንደ ተወው አላወቀም ነበር።