የባቢሎን ንጉሥ ስለ እነርሱ ሰማ፤ እጆቹም በድን ሆኑ፤ ጭንቀት ይዞታል፤ ምጥ እንደ ያዛት ሴት ታምሟል።
እስኪ ጠይቁ፤ ተመልከቱም፤ ወንድ መውለድ ይችላል? ታዲያ ወንድ ሁሉ ምጥ እንደ ያዛት ሴት፣ እጁን በሆዱ ላይ አድርጎ፣ የሰውስ ሁሉ ፊት ጠቍሮ የማየው ለምንድን ነው?
እነሆ፤ እንደ ንስር ተወርውሮ ይወርድባታል፤ ክንፎቹንም በባሶራ ላይ ይዘረጋል፤ በዚያ ቀን የኤዶም ጦረኞች ልብ፣ በምጥ እንደ ተያዘች ሴት ልብ ይሆናል።
ደማስቆ ተዳከመች፤ ትሸሽም ዘንድ ወደ ኋላ ተመለሰች፤ ብርክ ያዛት፣ ምጥ እንደ ያዛት ሴት፣ ጭንቅና መከራ ዋጣት።
ከተማዪቱ ሙሉ በሙሉ መያዟን፣ ለባቢሎን ንጉሥ ለመንገር፣ አንዱ ወሬኛ ሌላውን ወሬኛ፣ አንዱ መልእክተኛ ሌላውን መልእክተኛ ወዲያው ወዲያው ይከተላል፤
ስለ እነርሱ ወሬ ደርሶናል፤ ክንዶቻችንም ዝለዋል፤ ጭንቀት ይዞናል፤ እንደምታምጥም ሴት ሆነናል።