Biblia Todo Logo
ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች
- ማስታወቂያዎች -



ኤርምያስ 50:39

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

“ስለዚህ የምድረ በዳ አራዊትና የጅብ መኖሪያ፣ የጕጕትም ማደሪያ ትሆናለች፤ ከእንግዲህ ወዲህ ማንም አይኖርባትም፤ ከትውልድ እስከ ትውልድም የሚቀመጥባት አይገኝም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

“የጃርት መኖሪያ፣ ረግረጋማ ቦታ አደርጋታለሁ፤ በጥፋትም መጥረጊያ እጠርጋታለሁ” ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር።

“ነገር ግን ሰባው ዓመት ከተፈጸመ በኋላ፣ የባቢሎንን ንጉሥና ሕዝቡን፣ የባቢሎናውያንንም ምድር ስለ በደላቸው እቀጣቸዋለሁ” ይላል እግዚአብሔር፤ “ለዘላለምም ባድማ አደርጋታለሁ፤

ከሰሜን አንድ መንግሥት መጥቶ ይወጋታል፤ ምድሯንም ባድማ ያደርጋል፤ የሚኖርባትም አይገኝም፤ ሰዎችና እንስሳትም ሸሽተው ይሄዳሉ።

ከአንቺ ለማእዘን የሚሆን ድንጋይ፣ ለመሠረትም የሚሆን ዐለት አይወሰድም፤ ለዘላለም ባድማ ትሆኛለሽ፤” ይላል እግዚአብሔር።

ከተሞቿ ሰው የማይኖርባቸው፣ ዝርም የማይልባቸው፣ ደረቅና ምድረ በዳ፣ ባድማ ምድርም ይሆናሉ።

እርሱም በብርቱ ድምፅ እንዲህ ብሎ ጮኸ፤ “ታላቂቱ ባቢሎን ወደቀች! ወደቀች! የአጋንንት መኖሪያ፣ የርኩሳን መናፍስት ሁሉ መጠጊያ፣ የርኩስና የአስጸያፊ ወፎች ሁሉ መጠለያ ሆነች።




ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች