እግዚአብሔር አምላካችን የተበቀለውን፣ ስለ ቤተ መቅደሱ የተበቀለውን በቀል፣ ከባቢሎን የመጡ ኰብላዮችና ስደተኞች፣ በጽዮን የሚናገሩትን ስሟቸው።
ከባቢሎን ውጡ፣ ከባቢሎናውያንም ሽሹ! ይህን በእልልታ አስታውቁ፤ ዐውጁት፤ እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ተናገሩ፤ “እግዚአብሔር ባሪያውን ያዕቆብን ተቤዥቶታል” በሉ።
ከየአቅጣጫው ጩኹባት፤ እጇን ትሰጣለች፤ ምሽጓም ይወድቃል፤ ቅጥሮቿ ይፈርሳሉ። ይህ የእግዚአብሔር በቀል ነውና፣ እርሷን ተበቀሏት፤ በሌሎቹ ላይ እንዳደረገችውም አድርጉባት።
“ሕዝቤ ሆይ፤ ከመካከሏ ውጡ! ሕይወታችሁን አትርፉ! ከአስፈሪው የእግዚአብሔር ቍጣ አምልጡ።
“ከባቢሎን ሸሽታችሁ ውጡ! ፈጥናችሁም ሕይወታችሁን አትርፉ! በኀጢአቷ ምክንያት አትጥፉ። የእግዚአብሔር የበቀል ጊዜ ነው፤ እርሱም የሥራዋን ይከፍላታል።
ዮድ በሀብቷ ሁሉ ላይ፣ ጠላት እጁን ዘረጋ፤ ወደ ጉባኤህ እንዳይገቡ የከለከልሃቸው፣ ጣዖት የሚያመልኩ አሕዛብ፣ ወደ መቅደሷ ሲገቡ አየች።
ይልቁንም በሰማይ አምላክ ላይ በመታበይ፣ ራስህን ከፍ ከፍ አደረግህ፤ የመቅደሱን መጠጫዎች አስመጣህ፤ አንተና መኳንንትህ፣ ሚስቶችህና ቍባቶችህም የወይን ጠጅ ጠጣችሁባቸው፤ ማየት፣ መስማት፣ ማስተዋልም የማይችሉትን የብርና የወርቅ፣ የናስና የብረት፣ የዕንጨትና የድንጋይ አማልክትን አመሰገንህ። ሕይወትህንና መንገድህን ሁሉ በእጁ የያዘውን አምላክ ግን አላከበርህም።
ቃል ኪዳኔን ስላፈረሳችሁ፣ በላያችሁ ሰይፍ በማምጣት እበቀላችኋለሁ፤ በከተሞቻችሁ ውስጥ በምትሰበሰቡበት ጊዜ ቸነፈር እሰድድባችኋለሁ፤ ለጠላትም እጅ ዐልፋችሁ ትሰጣላችሁ።
የሚያብረቀርቅ ሰይፌን ስዬ፣ እጄ ለፍርድ ስትይዘው፣ ባላጋራዎቼን እበቀላቸዋለሁ፤ የሚጠሉኝንም እንደ ሥራቸው እከፍላቸዋለሁ።