“የሚያስፈራና የሚያስደነግጥ ነገር በምድሪቱ ላይ ሆኗል፤
ሰማያት ሆይ፤ ስሙ! ምድር ሆይ፤ አድምጪ! እግዚአብሔር እንዲህ ሲል ተናግሯልና፤ “ልጆች ወለድሁ፣ አሳደግኋቸውም፤ እነርሱ ግን ዐመፁብኝ።
ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “እስኪ አሕዛብን፣ ‘እንዲህ ዐይነት ነገር በመካከላችሁ ተሰምቶ ያውቃል?’ ብላችሁ ጠይቁ። ድንግሊቱ እስራኤል፣ እጅግ ክፉ ነገር አድርጋለች።
ሰማያት ሆይ፤ በዚህ ተገረሙ፤ በታላቅ ድንጋጤም ተንቀጥቀጡ፤” ይላል እግዚአብሔር።
በኢየሩሳሌም ባሉ ነቢያትም ላይ፣ የሚዘገንን ነገር አይቻለሁ፤ ያመነዝራሉ፤ በመዋሸትም ይኖራሉ፤ ማንም ከክፋቱ እንዳይመለስ፣ የክፉዎችን እጅ ያበረታሉ፤ በእኔ ዘንድ ሁሉም እንደ ሰዶም፣ ነዋሪዎቿም እንደ ገሞራ ናቸው።”
በእስራኤል ቤት የሚሰቀጥጥ ነገር አይቻለሁ፤ በዚያ ኤፍሬም ዘማዊ ሆነ፤ እስራኤልም ረከሰ።