“ተነሡ፣ ተዘልሎ የተቀመጠውን፣ በራሱ ተማምኖ የሚኖረውን ሕዝብ ውጉ፤” ይላል እግዚአብሔር፤ “መዝጊያና መቀርቀሪያ በሌለው፤ ለብቻው በሚኖረው ሕዝብ ላይ ዝመቱ።
ነፍሳችን የቅንጡዎች ስድብ፣ የትዕቢተኞችም ንቀት እጅግ በዝቶባታል።
እንግዲህ፣ ክፉዎች ይህን ይመስላሉ፤ ሁልጊዜ ግድ የለሽና ሀብት በሀብት ናቸው።
እናንተ ትዕቢት የወጠራችሁ ሴቶች ተንቀጥቀጡ፤ እናንተ ተደላድላችሁ የምትኖሩ ሴቶች ልጆች፣ በፍርሀት ተርበትበቱ! ልብሳችሁን አውልቁ፤ ወገባችሁን በማቅ ታጠቁ።
እናንተ ትዕቢት የወጠራችሁ ሴቶች፣ ተነሡ፤ ድምፄን ስሙ፤ እናንተ ተደላድላችሁ የምትኖሩ ሴቶች ልጆች ሆይ፤ የምነግራችሁን አድምጡ!
ምድረ በዳውና ከተሞቹ ድምፃቸውን ከፍ ያድርጉ፤ ቄዳር ያለችበት መንደር ደስ ይበለው፤ የሴላ ሕዝቦች በደስታ ይዘምሩ፤ ከተራሮችም ራስ ላይ ይጩኹ።
“አሁንም አንቺ ቅምጥል ፍጡር፣ በራስሽ ተማምነሽ የምትቀመጪ፣ በልብሽም፣ ‘እኔ ነኝ፣ ከእኔ በቀር ሌላ የለም፤ ከእንግዲህ መበለት አልሆንም፤ የወላድ መካንም አልሆንም’ የምትይ ስሚ!
“ሞዓብ በአንቡላው ላይ እንዳረፈ የወይን ጠጅ፣ ከልጅነት ጀምሮ የተረጋጋ ነበረ፤ ከዕቃ ወደ ዕቃ አልተገላበጠም፤ በምርኮም አልተወሰደም፤ ቃናው እንዳለ ነው፤ መዐዛውም አልተለወጠም።
“ ‘በዚያ ቀን ከእኔ ዘንድ መልእክተኞች በመርከብ ወጥተው ያለ ሥጋት ከተቀመጠችበት ሁኔታ ለማውጣት ኢትዮጵያን ያስፈራሯታል፤ ግብጽ በጨለማ በምትዋጥበት ቀን ጭንቅ ይይዛቸዋል፤ ቀኑ በርግጥ ይመጣልና።
እንዲህም ትላለህ፤ “ቅጥር የሌላቸውን መንደሮች ምድር እወራለሁ፤ ሁሉም ያለ ቅጥር፣ ያለ በርና ያለ ብረት መወርወሪያ የሚኖረውን፣ ሰላማዊና ያለ ሥጋት የተቀመጠውን ሕዝብ እወጋለሁ፤
በማጎግና ያለ ሥጋት በባሕር ዳርቻ በሚኖሩት ላይ እሳት እሰድዳለሁ፤ እነርሱም እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።
ብቻቸውን በዱር ውስጥ፣ በለመለመ መስክ የሚኖሩትን፣ የርስትህ መንጋ የሆኑትን፣ ሕዝብህን በበትርህ ጠብቅ፤ እንደ ቀድሞው ዘመን፣ በባሳንና በገለዓድ ይሰማሩ።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ምንም ኀይለኞችና ብዙዎች ቢሆኑም፣ ይቈረጣሉ፤ ይጠፋሉም። ይሁዳ ሆይ፤ ከዚህ በፊት ባስጨንቅህም፣ ከእንግዲህ አላስጨንቅህም።
ያለ ሥጋት የኖረች፣ ደስተኛዪቱ ከተማ ይህች ናት፤ እርሷም በልቧ፣ “እኔ ብቻ ነኝ! ከእኔ በቀር ማንም የለም” ያለች፣ ታዲያ እንዴት የዱር አራዊት የሚመሰጉባት፣ ባድማ ሆና ቀረች? በአጠገቧ የሚያልፉ ሁሉ፣ ያፌዙባታል፤ እጃቸውንም በንቀት ያወዛውዙባታል።
ከዐለታማ ተራሮች ጫፍ ሆኜ አየዋለሁ፤ በከፍታዎቹም ላይ ሆኜ እመለከተዋለሁ፤ ተለይቶ የሚኖረውን፣ ራሱንም ከሌሎች ሕዝቦች ጋራ የማይቈጥረውን ሕዝብ አያለሁ።
ስለዚህ እስራኤል ብቻውን ያለ ሥጋት ይኖራል፤ የሰማያት ጠል በሚወርድበት፣ እህልና የወይን ጠጅ ባለበት ምድር፣ የያዕቆብን ምንጭ የሚነካው የለም።