ክፉኛ እያለቀሱ፣ ወደ ሉሒት ሽቅብ ይወጣሉ፤ ስለ ደረሰባቸውም ጥፋት መራራ ጩኸት እያሰሙ፣ ወደ ሖሮናይም ቍልቍል ይወርዳሉ።
ልቤ ስለ ሞዓብ አለቀሰ፤ ስደተኞቿም እስከ ዞዓር፣ እስከ ዔግላት ሺሊሺያ ሸሹ፤ እንባቸውን እያፈሰሱ ወደ ሉሒት ወጡ፤ በሖሮናይም መንገድም፣ ስለ ጥፋታቸው ዋይ እያሉ ነጐዱ።
ከሖሮናይም የሚወጣውን ጩኸት፣ የመውደምና የታላቅ ጥፋት ድምፅ ስሙ!
ሞዓብ ትሰበራለች፤ ልጆቿም ጩኸት ያሰማሉ።