“እንዴት ተንኰታኰተ! ምንኛስ አለቀሱ! ሞዓብ እንዴት ዐፍሮ ጀርባውን አዞረ! ሞዓብ የመሰደቢያ፣ በዙሪያው ላሉትም ሁሉ የሽብር ምልክት ሆነ።”
የእስራኤል ቤት፤ በቤቴል ታምኖ እንዳፈረ ሁሉ፣ ሞዓብም በካሞሽ ያፍራል።
በዙሪያው የምትኖሩ ሁሉ፤ ዝናውን የምታውቁ ሁሉ አልቅሱለት፤ ‘ብርቱው ከዘራ፣ የከበረው በትር እንዴት ሊሰበር ቻለ’ በሉ።
በሕዝብ ተሞልታ የነበረችው ከተማ፣ እንዴት የተተወች ሆና ቀረች! በሕዝቦች መካከል ታላቅ የነበረችው፣ እርሷ እንዴት እንደ መበለት ሆነች! በአውራጃዎች መካከል ልዕልት የነበረችው፣ አሁን ባሪያ ሆናለች።
ጌታ የጽዮንን ሴት ልጅ፣ በቍጣው ደመና እንዴት ጋረዳት! ከሰማይ ወደ ምድር፣ የእስራኤልን ክብር ወርውሮ ጣለው፤ በቍጣው ቀን፣ የእግሩን መቀመጫ አላስታወሰም።
ወርቁ እንዴት ደበሰ! ንጹሑስ ወርቅ እንዴት ተለወጠ! የከበሩ ድንጋዮች፣ በየመንገዱ ዳር ተበታትነዋል።