ከሞዓብ የአትክልት ቦታና ዕርሻ፣ ሐሤትና ደስታ ርቋል፤ የወይን ጠጅ ከመጭመቂያው እንዳይወርድ አድርቄዋለሁ፤ በእልልታ የሚጨምቀውም አይገኝም፤ በዚያ ድምፅ ቢሰማም፣ የእልልታ ድምፅ አይደለም።
ከሩብ ጋሻ የወይን ቦታ አንድ የባዶስ መስፈሪያ ያህል የወይን ጭማቂ ብቻ ይገኛል፤ አንድ የቆሮስ መስፈሪያ ዘር ተዘርቶ አንድ የኢፍ መስፈሪያ እህል ብቻ ይሰጣል።”
በዚያ ቀን ሺሕ ሰቅል ብር የሚያወጣ አንድ ሺሕ የወይን ተክል የነበረበት ቦታ ሁሉ፣ ኵርንችትና እሾኽ ብቻ ይሆናል።
ሕዝብን አበዛህ፤ ደስታቸውንም ጨመርህ፤ ሰዎች ምርትን ሲሰበስቡ፣ ምርኮንም ሲከፋፈሉ ደስ እንደሚላቸው ሁሉ፣ እነርሱም በፊትህ ደስ ይላቸዋል።
የሚበላ ምግብ፣ ከዐይናችን ፊት፣ ደስታና ተድላ፣ ከአምላካችን ቤት አልተቋረጠብንምን?
እናንተ ሰካራሞች፤ ተነሡ፤ አልቅሱ፤ እናንተ የወይን ጠጅ ጠጪዎች ሁሉ፤ ዋይ በሉ፤ ስለ አዲሱ የወይን ጠጅ ዋይ ብላችሁ አልቅሱ፤ አፋችሁ ላይ እንዳለ ተነጥቃችኋልና።
በየወይኑ ዕርሻ ሁሉ ወየው ተብሎ ይለቀሳል፤ እኔ በመካከላችሁ ዐልፋለሁና፤” ይላል እግዚአብሔር።
አንድ ሰው ሃያ መስፈሪያ ወደሚሆን የእህል ክምር በመጣ ጊዜ ዐሥር ብቻ አገኘ፤ ዐምሳ ማድጋ የወይን ጠጅ ለመቅዳት ወደ መጭመቂያው በሄደ ጊዜ ሃያ ብቻ አገኘ።