Biblia Todo Logo
ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች
- ማስታወቂያዎች -



ኤርምያስ 48:11

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

“ሞዓብ በአንቡላው ላይ እንዳረፈ የወይን ጠጅ፣ ከልጅነት ጀምሮ የተረጋጋ ነበረ፤ ከዕቃ ወደ ዕቃ አልተገላበጠም፤ በምርኮም አልተወሰደም፤ ቃናው እንዳለ ነው፤ መዐዛውም አልተለወጠም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

16 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ነፍሳችን የቅንጡዎች ስድብ፣ የትዕቢተኞችም ንቀት እጅግ በዝቶባታል።

አካሄዳቸውን አልቀየሩምና፣ እግዚአብሔርንም አልፈሩትምና፣ ከጥንት ጀምሮ በዙፋኑ ላይ ያለ አምላክ፣ ሴላ ሰምቶ ያዋርዳቸዋል።

አላዋቂዎችን ስድነታቸው ይገድላቸዋል፤ ሞኞችንም መታለላቸው ያጠፋቸዋል፤

የሞዓብን መዘባነን፣ እጅግ መታበዩንና ኵራቱን፣ እብሪቱንና ስድነቱን ሰምተናል፤ ትምክሕቱ ግን ከንቱ ነው!

ምድር ፈጽሞ ባድማ ትሆናለች፤ ጨርሶም ትበዘበዛለች፤ እግዚአብሔር ይህን ቃል ተናግሯልና።

የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር በዚህ ተራራ ላይ፣ ለሕዝብ ሁሉ ታላቅ የምግብ ግብዣ፣ የበሰለ የወይን ጠጅ ድግስ፣ ማለፊያ ጮማና ምርጥ የወይን ጠጅ ያዘጋጃል።

ተመችቶሽ በነበረ ጊዜ አስጠነቀቅሁሽ፤ አንቺ ግን፣ ‘አልሰማም’ አልሽ፤ ከትንሽነትሽ ጀምሮ መንገድሽ ይኸው ነበር፤ ቃሌንም አልሰማሽም።

ስለዚህ ዕቃውን የሚገለብጡ ሰዎችን የምልክበት ጊዜ ይመጣል፤” ይላል እግዚአብሔር። “እነርሱም ይደፉታል፤ ዕቃውን ባዶ ያስቀራሉ፤ ማንቈርቈሪያዎቹንም ይሰባብራሉ።

“ስለ ሞዓብ ትዕቢት፣ ስለ እብሪቱና ስለ ኵራቱ፣ ስለ ትምክሕቱና ስለ መጓደዱ፣ ስለ ልቡም ማበጥ ሰምተናል።

“የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር በላን፣ አድቅቆ ፈጨን፤ እንደ ባዶ ማድጋ አደረገን፤ እንደ ዘንዶ ዋጠን፣ እንደ ጣፋጭ በልቶን ሆዱን ሞላ፤ በኋላም አንቅሮ ተፋን፤

ተበዝብዛለች፤ ተዘርፋለች፤ ተራቍታለች። ልብ ቀልጧል፤ ጕልበት ተብረክርኳል፤ ሰውነት ተንቀጥቅጧል፤ ፊት ሁሉ ገርጥቷል።

አጥፊዎች ባድማ ቢያደርጓቸውም፣ የወይን ተክል ቦታቸውን ቢያጠፉባቸውም፣ እንደ እስራኤል ክብር ሁሉ፣ እግዚአብሔር የያዕቆብንም ክብር ይመልሳል።

በዚያ ዘመን ኢየሩሳሌምን በመብራት እፈትሻለሁ፤ ተንደላቅቀው የሚኖሩትን፣ በዝቃጩ ላይ እንደ ቀረ የወይን ጠጅ የሆኑትን፣ ‘ክፉም ይሁን መልካም፣ እግዚአብሔር ምንም አያደርግም’ የሚሉትን ቸልተኞች እቀጣለሁ።

ሰላም አለ በሚሉ አሕዛብ ላይ ግን በጣም ተቈጥቻለሁ፤ በመጠኑ ተቈጥቼ ሳለሁ፣ እነርሱ ግን ጥፋቱ እንዲብስ አደረጉ።’




ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች