“ትልቁንና ትንሹን ጋሻ አዘጋጁ፤ ለውጊያም ውጡ!
ማእዱን አሰናዱ፤ ምንጣፉን አነጠፉ፤ በሉ፤ ጠጡ! እናንተ ሹማምት ተነሡ፤ ጋሻውን በዘይት ወልውሉ!
“ይህን በግብጽ ተናገር፤ በሚግዶልም አሰማ፤ በሜምፊስና በጣፍናስም እንዲህ ብለህ ዐውጅ፤ ‘በቦታችሁ ቁሙ፤ ተዘጋጁም፤ በዙሪያችሁ ያሉትን ሰይፍ ይበላቸዋልና።’
በሕዝቦች መካከል ይህን ዐውጁ፤ ለጦርነት ተዘጋጁ፤ ተዋጊዎችን አነሣሡ፤ ጦረኞችም ሁሉ ቀርበው ያጥቁ።
ነነዌ ሆይ፤ አጥቂ መጥቶብሻል፤ ምሽግሽን ጠብቂ፤ መንገድሽን ሰልዪ፤ ወገብሽን ታጠቂ፤ ኀይልሽን ሁሉ አሰባስቢ።
ለከበባው ውሃ ቅጅ፤ መከላከያሽን አጠናክሪ፤ የሸክላውን ዐፈር ፈልጊ፤ ጭቃውን ርገጪ፤ ጡቡንም ሥሪ።