“ድንግሊቱ የግብጽ ሴት ልጅ ሆይ፤ ወደ ገለዓድ ውጪ፤ የሚቀባ መድኀኒትም አምጪ፤ ነገር ግን መድኀኒት የምታበዢው በከንቱ ነው፤ ፈውስ አታገኚም።
ምግባቸውን ለመብላት ተቀመጡ፤ አሻግረው ሲመለከቱም ከገለዓድ የሚመጡ እስማኤላውያን ነጋዴዎች የግመል ጓዝ አዩ። ነጋዴዎቹ ሽቱ፣ በለሳን ከርቤ በግመሎቻቸው ጭነው ወደ ግብጽ የሚወርዱ ነበሩ።
ከዚህ በኋላ አባታቸው እስራኤል እንዲህ አላቸው፤ “ነገሩ እንዲህ ከሆነስ ይህን አድርጉ፤ ምድሪቱ ከምታፈራው ምርጥ ነገሮች ጥቂት በለሳን፣ ጥቂት ማር፣ ሽቱ፣ ከርቤ፣ ተምርና አልሙን በየስልቻችሁ ይዛችሁ ለዚያ ሰው እጅ መንሻ ውሰዱለት።
“አንቺ የባቢሎን ድንግል ልጅ ሆይ፤ ውረጂ፤ በትቢያ ላይ ተቀመጪ፤ አንቺ የባቢሎናውያን ልጅ ሆይ፤ ከዙፋንሽ ውረጂ፤ መሬት ላይ ተቀመጪ፤ ከእንግዲህ ውብ ወይም ለግላጋ፣ ተብለሽ አትጠሪም።
“ይህን ቃል እንዲህ ብለህ ንገራቸው፤ “ ‘ድንግሊቱ ልጄ፣ ሕዝቤ፣ በታላቅ ስብራት፣ በብርቱ ቍስል ተመትታለችና ዐይኖቼ ቀንና ሌሊት፣ ሳያቋርጡ እንባ ያፈስሳሉ
“የጐዳና ምልክት አቁሚ፤ መንገድ አመልካች ትከዪ፤ የምትሄጂበትን መንገድ፣ አውራ ጐዳናውን አስተውዪ፤ ድንግሊቱ እስራኤል ሆይ፤ ተመለሺ፤ ወደ ከተሞችሽም ግቢ።
የእስራኤል ድንግል ሆይ፤ እንደ ገና ዐንጽሻለሁ፤ አንቺም ትታነጺአለሽ፤ ከበሮችሽንም እንደ ገና አንሥተሽ፣ ከሚፈነጥዙት ጋራ ትፈነድቂአለሽ።
ባቢሎን በድንገት ወድቃ ትሰበራለች፤ ዋይ በሉላት! ምናልባት ልትፈወስ ስለምትችል፣ ለቍስሏ የሚቀባ መድኀኒት ፈልጉላት።
በገለዓድ የሚቀባ መድኀኒት የለምን? ወይስ በዚያ ሐኪም አልነበረምን? ለሕዝቤ ቍስል፣ ለምን ፈውስ አልተገኘም?
“ ‘ይሁዳና እስራኤል እንኳ ከአንቺ ጋራ ተገበያይተዋል፤ የሚኒትን ስንዴ፣ ጣፋጭ ቂጣ፣ ማር፣ ዘይትና በለሳን በማምጣት በሸቀጥሽ ይለውጡ ነበር።
ቍስሏ የማይሽር ነውና፤ ለይሁዳ ተርፏል፤ እስከ ሕዝቤ መግቢያ በር፣ እስከ ኢየሩሳሌም እንኳ ደርሷል።
ቍስልህን ሊፈውስ የሚችል የለም፤ ስብራትህም ለሞት የሚያደርስ ነው። ስለ አንተ የሰማ ሁሉ፣ በውድቀትህ ደስ ብሎት ያጨበጭባል፤ ወሰን የሌለው ጭካኔህ ያልነካው ማን አለና?
እውነት እልሃለሁ፤ ካስፈረደብህ ግን የመጨረሻዋን ሳንቲም እስክትከፍል ድረስ ከዚያ አትወጣም።