ለመልካም ሳይሆን ለክፉ እተጋባቸዋለሁና፤ በግብጽ የሚኖሩ አይሁድ ፈጽሞ እስኪጠፉ ድረስ በሰይፍና በራብ ይደመሰሳሉ።
የርስቴንም ቅሬታ እተዋቸዋለሁ፤ ለጠላቶቻቸው አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ፤ ለጠላቶቻቸውም ሁሉ ብዝበዛና ምርኮ ይሆናሉ።
እንግዲህ፣ እንድትነቅልና እንድታፈርስ፣ እንድታጠፋና እንድትገለብጥ፣ እንድታንጽና እንድትተክል በአሕዛብና በመንግሥታት ላይ ዛሬ ሾምሁህ።”
በዚህች ከተማ ላይ በጎ ሳይሆን ክፉ ለማድረግ ወስኛለሁ፤” ይላል እግዚአብሔር፤ ለባቢሎን ንጉሥ ትሰጣለች፤ እርሱም በእሳት ያጠፋታል።’
ልነቅላቸውና ላፈርሳቸው፣ ልገለብጣቸውና ላጠፋቸው፣ መከራም ላመጣባቸው እንደ ተጋሁ ሁሉ፣ ላንጻቸውና ልተክላቸው ደግሞ እተጋለሁ” ይላል እግዚአብሔር።
“ሂድና ለኢትዮጵያዊው አቢሜሌክ እንዲህ በለው፤ ‘የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ዕድገት ሳይሆን ጥፋት በማምጣት በዚህች ከተማ ላይ ቃሌን እፈጽማለሁ፤ በዚያ ጊዜ በዐይንህ እያየህ ይህ ይፈጸማል።
የፈራችሁት ሰይፍ በዚያ ያገኛችኋል፤ የሠጋችሁበት ራብ እስከ ግብጽ ድረስ ተከትሏችሁ ይመጣል፤ በዚያም ትሞታላችሁ።
ሄደው በግብጽ ለመቀመጥ የወሰኑትን የይሁዳ ቅሬታዎች ሁሉ እነጥቃለሁ፤ ሁሉም ይጠፋሉ፤ በግብጽ ምድር በሰይፍ ይወድቃሉ፤ በራብ ያልቃሉ፤ ከትንሽ እስከ ትልቅ በሰይፍና በራብ ይሞታሉ፤ የመነቀፊያና የድንጋጤ፣ የመረገሚያና የመዘባበቻ ምልክት ይሆናሉ።
ኢየሩሳሌምን እንደ ቀጣሁ፣ በግብጽ የሚኖሩትን በሰይፍ፣ በራብና በቸነፈር እቀጣለሁ፤
ወደ ግብጽ የመጡት የይሁዳ ቅሬታዎች ወደ ይሁዳ ለመመለስ ቢመኙም ከጥቂት ስደተኞች በቀር አምልጦ ወይም ተርፎ ወደ ይሁዳ የሚመለስ አንድም ሰው አይኖርም።’ ”
ነገር ግን ለሰማይዋ ንግሥት ማጠንና የመጠጥ ቍርባን ማፍሰስ ከተውን ወዲህ ሁሉን ነገር ዐጥተናል፤ በሰይፍና በራብም እያለቅን ነው።”
ስለዚህ የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ እንዲህ ይላል፤ “እነሆ፤ ይህን ሕዝብ መራራ ምግብ አበላዋለሁ፤ የተመረዘንም ውሃ አጠጣዋለሁ።
እነርሱንም ሆነ አባቶቻቸውን በማያውቋቸው ሕዝቦች መካከል እበትናቸዋለሁ፤ እስካጠፋቸውም ድረስ በሰይፍ አሳድዳቸዋለሁ።”
ከሕዝብሽ ሢሶው በቸነፈር ይሞታል፤ በመካከልሽም በራብ ያልቃል፤ ሌላው ሢሶ ከቅጥርሽ ውጪ በሰይፍ ይወድቃል፤ የቀረውን ሢሶ ደግሞ ለነፋስ እበትናለሁ፤ በተመዘዘም ሰይፍ አሳድደዋለሁ።
ፍጻሜ መጥቷል! ፍጻሜ መጥቷል! በአንቺ ላይ ተነሣሥቷል፤ እነሆ፤ ደርሷል!
አምላካችን እግዚአብሔር በሚያደርገው ሁሉ ጻድቅ ነውና፣ በእኛ ላይ እግዚአብሔር ጥፋት ከማምጣት አልተመለሰም፤ እኛም አልታዘዝነውም።
“እነሆ፤ የጌታ እግዚአብሔር ዐይኖች፣ በኀጢአተኛ መንግሥት ላይ ናቸው፤ ከምድር ገጽ፣ ፈጽሜ አጠፋዋለሁ፤ የያዕቆብን ቤት ግን፣ ሙሉ በሙሉ አልደመስስም፤” ይላል እግዚአብሔር።