በግብጽ ሰሜናዊ ክፍል በሚግዶል፣ በጣፍናስና በሜምፊስ እንዲሁም በግብጽ ደቡባዊ ክፍል ስለሚኖሩት የአይሁድ ሕዝብ እንዲህ የሚል ቃል ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ኤርምያስ መጣ፤
የፈትሩሲማውያን፣ ፍልስጥኤማውያን የተገኙባቸው፣ የከስሉሂማውያንና የቀፍቶሪማውያን አባት ነበረ።
“እስራኤላውያን ተመልሰው በሚግዶልና በባሕሩ መካከል ባለው በፊሀሒሮት አጠገብ እንዲሰፍሩ ንገራቸው፤ በበኣልዛፎንም አንጻር በባሕሩ አጠገብ ይስፈሩ።
በዚያ ቀን፣ ጌታ እጁን ዘርግቶ እንደ ገና የተረፈውን የሕዝቡን ቅሬታ ከአሦር፣ ከግብጽ፣ ከጳትሮስ፣ ከኢትዮጵያ፣ ከኤላም፣ ከባቢሎን፣ ከሐማትና ከባሕር ጠረፍ ምድር ይሰበስባል።
የጣኔዎስ አለቆች ተሞኝተዋል፤ የሜምፊስ ሹማምት ተታልለዋል፤ የሕዝቧ ዋና ዋናዎች፣ ግብጽን አስተዋታል።
ደግሞም የሜምፊስና የጣፍናስ ሰዎች፣ መኻል ዐናትሽን ላጩሽ።
“ ‘ነገር ግን ከመበላሸቱ የተነሣ ሊበላ እንደማይቻለው እንደ መጥፎ በለስ’ ይላል እግዚአብሔር፤ ‘የይሁዳን ንጉሥ ሴዴቅያስንና ባለሥልጣኖቹን እንዲሁም በኢየሩሳሌም የቀሩትንም ሆነ በግብጽ የሚኖሩትን፣ እንዲሁ አደርግባቸዋለሁ።
በግብጽ ምድር የሚገኙትን የፀሓይ አምላክ ቤተ ጣዖት ሐውልቶች ይሰባብራል፤ የግብጽንም አማልክት ቤተ ጣዖቶች በእሳት ያቃጥላል።’ ”
ሚስቶቻቸው ለሌሎች አማልክት ማጠናቸውን ያወቁ ወንዶች ሁሉና በዚያ የነበሩት ሴቶች ሁሉ ይህም ማለት በሰሜንና በደቡብ ግብጽ የሚኖረው ሕዝብ ሁሉ ታላቅ ጉባኤ ሆነው ለኤርምያስ እንዲህ አሉት፤
“ይህን በግብጽ ተናገር፤ በሚግዶልም አሰማ፤ በሜምፊስና በጣፍናስም እንዲህ ብለህ ዐውጅ፤ ‘በቦታችሁ ቁሙ፤ ተዘጋጁም፤ በዙሪያችሁ ያሉትን ሰይፍ ይበላቸዋልና።’
እናንተ በግብጽ የምትኖሩ ሆይ፤ በምርኮ ለመወሰድ ጓዛችሁን አሰናዱ፤ ሜምፊስ ፈራርሳ፣ ሰው የማይኖርባት ባድማ ትሆናለችና።
ስለዚህ በአንተ ላይ ተነሥቻለሁ፤ በወንዞችህ ላይ ተነሥቻለሁ፤ የግብጽንም ምድር ከሚግዶል እስከ አስዋን ከዚያም እስከ ኢትዮጵያ ወሰን ድረስ ፍርስራሽና ባድማ አደርጋታለሁ።
ከተማረኩበት አመጣቸዋለሁ፤ ወደ አባቶቻቸው ምድር ወደ ጳትሮስ እመልሳቸዋለሁ።
“ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ ‘ጣዖታትን አጠፋለሁ፤ በሜምፊስ ያሉትን ምስሎች እደመስሳለሁ። ከእንግዲህ በግብጽ ገዥ አይኖርም፣ በምድሪቱም ላይ ፍርሀት እሰዳለሁ።
ጳትሮስን ባድማ አደርጋለሁ፤ በጣኔዎስ ላይ እሳት እለኵሳለሁ፤ በቴብስ ላይ ቅጣት አመጣለሁ።
በግብጽ ላይ እሳት አነድዳለሁ፤ ሲን በጭንቅ ትናጣለች፤ ቴብስ በማዕበል ትወሰዳለች፤ ሜምፊስ በማያቋርጥ ጭንቀት ውስጥ ትገባለች።
የግብጽን ቀንበር በምሰብርበት ጊዜ፣ በጣፍናስ ቀኑ ይጨልማል፤ ከዚያም የተኵራራችበት ብርታት ይንኰታኰታል። በደመና ትሸፈናለች፤ መንደሮቿም ይማረካሉ።
ከጥፋት ቢያመልጡም እንኳ፣ ግብጽ ትሰበስባቸዋለች፤ ሜምፎስም ትቀብራቸዋለች። የብር ሀብታቸውን ዳዋ ያለብሰዋል፤ ድንኳኖቻቸውንም እሾኽ ይወርሳቸዋል።