ከዚያም ተነሥተው ሄዱ፤ ወደ ግብጽም በማምራት በቤተ ልሔም አጠገብ ባለችው በጌሮት ከመዓም ዐረፉ፤
ደግሞም፣ ‘ጦርነት ወደማናይበት፣ የመለከት ድምፅ ወደማንሰማበትና ወደማንራብበት ወደ ግብጽ ምድር ሄደን በዚያ እንኖራለን’ ብትሉ፣
“እናንተ የይሁዳ ቅሬታ ሆይ፤ እግዚአብሔር፤ ‘ወደ ግብጽ አትሂዱ’ ብሏችኋል፤ እኔም ዛሬ እንዳስጠነቀቅኋችሁ በርግጥ ዕወቁ፤
ነገር ግን፣ የቃሬያ ልጅ ዮሐናንና የጦር መኰንኖቹ ሁሉ፣ በይሁዳ ምድር ለመቀመጥ ከተበተኑበት ከአሕዛብ ሁሉ መካከል የተመለሱትን የይሁዳን ቅሬታዎች ሁሉ ይዘው ሄዱ፤
የእግዚአብሔርንም ቃል ባለመታዘዝ ወደ ግብጽ ገቡ፤ ዘልቀውም እስከ ጣፍናስ ድረስ ሄዱ።