Biblia Todo Logo
ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች
- ማስታወቂያዎች -



ኤርምያስ 38:22

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በይሁዳ ቤተ መንግሥት የቀሩ ሴቶች ሁሉ ወደ ባቢሎናውያን ባለሥልጣኖች ይወሰዳሉ፤ ሴቶቹም እንዲህ ይላሉ፤ “ ‘እነዚያ የተማመንህባቸው ወዳጆችህ፣ አሳሳቱህ፤ አሸነፉህ። እግርህ ጭቃ ውስጥ ተሰንቅሯል፤ ወዳጆችህ ጥለውህ ሄደዋል።’

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

22 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ወንድሞቼ ግን እንደማያዛልቅ ጅረት፣ ለጊዜው ሞልቶ እንደሚፈስስ ወንዝ የማይታመኑ ናቸው፤

እንጀራዬን የበላ፣ የምተማመንበትም የቅርብ ወዳጄ፣ ተረከዙን አነሣብኝ።

ከረግረግ አውጣኝ፤ እሰጥም ዘንድ አትተወኝ፤ ከጥልቅ ውሃ፣ ከእነዚያ ከሚጠሉኝ ታደገኝ።

የእግር መቆሚያ በሌለው፣ በጥልቅ ረግረግ ውስጥ ሰጥሜአለሁ፤ ወደ ጥልቅ ውሃ ገባሁ፤ ሞገዱም አሰጠመኝ።

በጣዖት የሚታመኑ ግን፣ ምስሎችን፣ ‘አምላኮቻችን ናችሁ’ የሚሉ፣ ወደ ኋላቸው ይመለሳሉ፤ ፈጽመው ይዋረዳሉም።

ልዩ ወዳጆች እንዲሆኑሽ ያስተማርሻቸው፣ ባለሥልጣን ሲሆኑብሽ ምን ትያለሽ? እንደምትወልድ ሴት፣ ምጥ አይዝሽምን?

“በየቦታው ሽብር አለ፤ አውግዙት፤ እናውግዘው፤” ብለው ብዙ ሲያንሾካሽኩ ሰማሁ፤ መውደቄን በመጠባበቅ፣ ባልንጀሮቼ የነበሩ ሁሉ፣ “ይታለል ይሆናል፣ ከዚያም እናሸንፈዋለን፤ እንበቀለዋለንም” ይላሉ።

ሐሰተኛ ትንቢት ስለሚነግሯችሁ፣ ‘የባቢሎንን ንጉሥ አታገለግሉም’ የሚሏችሁን ነቢያት አትስሙ፤

‘እኔ አልላክኋቸውም’ ይላል እግዚአብሔር ‘የሐሰት ትንቢት በስሜ ይናገራሉ፤ ስለዚህ እናንተንና ትንቢት የሚናገሩላችሁን ነቢያት አሳድዳለሁ፤ እናንተም ትጠፋላችሁ።’ ”

ንጉሡም ሴዴቅያስ ኤርምያስን፣ “ወደ ባቢሎን የኰበለሉት አይሁድ እንዲያላግጡብኝ፣ ባቢሎናውያን ለእነርሱ አሳልፈው ይሰጡኛል ብዬ እፈራለሁ” አለው።

እጅህን ለመስጠት እንቢ ብትል ግን፣ እግዚአብሔር የገለጠልኝ ነገር ይህ ነው፤

እስማኤል በምጽጳ የቀረውን ሕዝብ ሁሉ ምርኮኛ አደረገ፤ እነርሱም የባቢሎን የክብር ዘበኞች አዛዥ ናቡዘረዳን የአኪቃምን ልጅ ጎዶልያስን በላያቸው ገዥ አድርጎ የሾመባቸው የንጉሡ ሴቶች ልጆችና በዚያ የቀሩት ሌሎች ሰዎች ሁሉ ነበሩ። የናታንያ ልጅ እስማኤል እነዚህን ማርኮ ወደ አሞናውያን ለመሻገር ተነሣ።

በተጨማሪም ወንዶችን፣ ሴቶችንና ሕፃናትን እንዲሁም የክብር ዘበኞች አዛዥ ናቡዘረዳን በአኪቃም ልጅና በሳፋን የልጅ ልጅ በጎዶልያስ እጅ የተዋቸውን የንጉሡን ሴቶች ልጆች፣ ነቢዩ ኤርምያስንና የኔርያን ልጅ ባሮክን ወሰዷቸው፤

ቅጥረኞች ወታደሮቿም እንደ ሠቡ ወይፈኖች ናቸው፤ የሚቀጡበት ጊዜ ስለ ደረሰ፣ ጥፋታቸው ስለ ተቃረበ፣ እነርሱም ወደ ኋላ ተመልሰው በአንድነት ይሸሻሉ፤ በቦታቸውም ጸንተው ሊቋቋሙ አይችሉም።

ነገር ግን ይህ የማየው ምንድን ነው? እጅግ ፈርተዋል፤ ወደ ኋላ እያፈገፈጉ ነው፤ ብርቱ ጦረኞቻቸው ተሸንፈዋል፤ ዘወር ብለውም ሳያዩ፣ በፍጥነት እየሸሹ ነው፤ በየቦታውም ሽብር አለ፣” ይላል እግዚአብሔር።

በምድሪቱ በሚኖሩት ላይ እጄን በምዘረጋበት ጊዜ፣ ዕርሻቸውና ሚስቶቻቸው ሳይቀሩ፣ ቤቶቻቸው ለሌሎች ይሆናሉ፤” ይላል እግዚአብሔር።

ስለዚህ ሚስቶቻቸውንም ለሌሎች ወንዶች እሰጣለሁ፤ ዕርሻዎቻቸውንም ለባዕዳን እሰጣለሁ፤ ከታናሹ እስከ ታላቁ ድረስ፣ ሁሉም ተገቢ ላልሆነ ጥቅም ይስገበገባሉ፤ ነቢያትና ካህናትም እንዲሁ፤ ሁሉም ያጭበረብራሉ።

“ከከፍታ ስፍራ እሳትን ላከ፤ ወደ ታች ወደ ዐጥንቶቼም ሰደደው፤ በእግሮቼ ላይ መረብ ዘረጋ፤ ወደ ኋላም ጣለኝ፤ ቀኑን ሙሉ በማድከም፣ ባዶ አድርጎ አስቀመጠኝ።

በሌሊት አምርራ ታለቅሳለች፤ እንባዋ በጕንጮቿ ላይ ይወርዳል፤ ከወዳጆቿ ሁሉ መካከል፣ የሚያጽናናት ማንም የለም፤ ባልንጀሮቿ ሁሉ ከድተዋታል፤ ጠላቶቿም ሆነዋል።

ሴቶች በጽዮን፣ ደናግል በይሁዳ ከተሞች ተደፈሩ።

ባልንጀራህን አትመን፤ በጓደኛህም አትታመን፤ በዕቅፍህ ለምትተኛዋ እንኳ፣ ስለምትነግራት ቃል ተጠንቀቅ።




ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች