የምንቀመጥበትም ቤት አልሠራንም፤ የወይን ቦታ፣ የዕርሻ ስፍራ ወይም የእህል ዘር የለንም።
ኤልሳዕ ግን እንዲህ አለው፤ “ያ ሰው ሊገናኝህ ከሠረገላው ሲወርድ፣ መንፈሴ ከአንተ ጋራ አልሄደምን? እንዲያው ለመሆኑ ጊዜው ገንዘብና ልብስ፣ የወይራ ዘይት ተክልና የወይን ተክል ቦታ፣ የበግና የከብት መንጋ፣ ወንድና ሴት አገልጋይ የሚቀበሉበት ነውን?
የጻድቅ ጥቂት ሀብት፣ ከክፉዎች ብዙ ጥሪት ይበልጣል።
ቤት አትሥሩ፤ ዘር አትዝሩ፤ ወይን አትትከሉ፤ ሁልጊዜ በድንኳን ኑሩ እንጂ ከእነዚህ ነገሮች አንዱም አይኑራችሁ፤ ይህም ሲሆን እንደ መጻተኛ በሆናችሁበት ምድር ረዥም ዘመን ትኖራላችሁ።’
ከዚህም በቀር አንተ ማርና ወተት ወደምታፈስሰው ምድር አላመጣኸንም፤ ወይም ዕርሻዎችንና የወይን ተክል ቦታዎች አላወረስኸንም። ታዲያ የእነዚህን ሰዎች ዐይን ታወጣለህን? በጭራሽ አንመጣም!”
ነገር ግን እውነተኛ መንፈሳዊነት ባለን ነገር ከመርካት ጋራ ትልቅ ትርፍ ነው።