ወደ እግዚአብሔር ቤት አመጣኋቸው፤ ወደ ሐናን ልጆች ክፍልም አስገባኋቸው፤ የሐናን አባት ጌዴልያም የእግዚአብሔር ሰው ነበረ። ክፍሉም በመኳንንቱ ክፍል አጠገብ፣ ከመዕሤያ ክፍል በላይ ነበር፤ መዕሤያም የበር ጠባቂው የሰሎም ልጅ ነበረ፤
ነገር ግን የእግዚአብሔር ቃል፣ የእግዚአብሔር ሰው ወደ ሆነው ወደ ሸማያ እንዲህ ሲል መጣ፤
ኢዮርብዓም መሥዋዕት ለማቅረብ በመሠዊያው አጠገብ ቆሞ ሳለ፣ በእግዚአብሔር ቃል ታዝዞ አንድ የእግዚአብሔር ሰው ከይሁዳ ወደ ቤቴል መጣ።
ያም ከመንገድ የመለሰው ነቢይ ይህን ሲሰማ፣ “ይህ የእግዚአብሔርን ቃል ያቃለለው ያ የእግዚአብሔር ሰው ነው፤ እግዚአብሔር ባስጠነቀቀው ቃል መሠረት አሳልፎ ሰጥቶት አንበሳ ሰብሮ ገድሎታል” አለ።
እርሷም ኤልያስን፤ “የእግዚአብሔር ሰው ሆይ፤ እኔ ምን አደረግሁህ? እዚህ የመጣኸው ኀጢአቴን አስታውሰህ ልጄን ለመግደል ነውን?” አለችው።
ከዚያም ሴቲቱ ኤልያስን፣ “አሁን የእግዚአብሔር ሰው መሆንህን፣ ከአንደበትህም የወጣው የእግዚአብሔር ቃል እውነት መሆኑን ዐወቅሁ” አለችው።
የእግዚአብሔርም ሰው ወጥቶ ለእስራኤል ንጉሥ፣ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ሶርያውያን እግዚአብሔር የኰረብታ እንጂ የሸለቆ አምላክ አይደለም ብለዋልና ይህን ስፍር ቍጥር የሌለው ሰራዊት በእጅህ አሳልፌ እሰጥሃለሁ፤ አንተም እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ታውቃለህ’ ” አለው።
ከዚያም ንጉሡ አንድ የዐምሳ አለቃ ከዐምሳ ወታደሮቹ ጋራ ወደ ኤልያስ ላከ። የዐምሳ አለቃውም ኤልያስ ወደ ተቀመጠበት ኰረብታ ጫፍ ወጥቶ፣ “አንተ የእግዚአብሔር ሰው፤ ንጉሡ፣ ‘ና ውረድ’ ይልሃል” አለው።
ከዚያም ካህኑ ዮዳሄ አንድ ሣጥን ወስዶ በመክደኛው ላይ ቀዳዳ አበጀለት፤ ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ በሚያስገባው በስተቀኝ በኩል በመሠዊያው አጠገብ አኖረው። በራፉን የሚጠብቁት ካህናትም ወደ እግዚአብሔር ቤት የሚመጣውን ገንዘብ በሙሉ በሣጥኑ ውስጥ ያስገቡ ነበር።
የክብር ዘበኞቹ አዛዥም ሊቀ ካህኑን ሠራያን፣ በማዕርግ ከርሱ ቀጥሎ ያለውን ካህኑን ሶፎንያስንና ሦስቱን የበር ጠባቂዎች እስረኛ አድርጎ ወሰዳቸው።
ስለዚህ ንዕማን ወረደ፤ የእግዚአብሔር ሰው እንደ ነገረውም በዮርዳኖስ ሰባት ጊዜ ብቅ ጥልቅ አለ፤ ሥጋውም እንደ ትንሽ ልጅ ሥጋ ሆነ፤ ነጻም።
የእግዚአብሔር ሰው የኤልሳዕ አገልጋይ ግያዝ፣ “ጌታዬ፤ ይህ ሶርያዊ ንዕማን ያመጣውን አለመቀበሉ አይደል፤ ሕያው እግዚአብሔርን! ተከትዬ ሄጄ ከርሱ አንድ ነገር ማግኘት አለብኝ” ብሎ ዐሰበ።
ስለዚህ የእስራኤል ንጉሥ የእግዚአብሔር ሰው የነገረውን ቦታ አስቃኘ፤ ኤልሳዕም ንጉሡን እንደዚህ ካሉት ቦታዎች ራሱን እንዲጠብቅ ከአንድ ሁለት ጊዜ በላይ አስጠነቀቀው።
በዚህ ጊዜ ንጉሡ እጁን ይደግፈው የነበረውን የጦር አለቃ፣ የቅጥሩ በር ኀላፊ አድርጎት ነበርና በበራፉ መተላለፊያ ላይ ሕዝቡ ሲጋፋ ረጋገጠው፤ ያ የእግዚአብሔር ሰው ንጉሡ ወደ እርሱ በመጣ ጊዜ አስቀድሞ እንደ ተናገረውም የጦር አለቃው ሞተ።
ንጉሡ በክንዱ ላይ የተደገፈውም የጦር አለቃ፣ የእግዚአብሔርን ሰው፣ “እንዲያው ለመሆኑ፣ እግዚአብሔር የሰማያትን መስኮቶች ቢከፍት እንኳ ይህ ሊሆን ይችላልን?” ሲል ጠየቀው። ኤልሳዕም፣ “ይህን አንተው ራስህ በዐይንህ ታየዋለህ፤ ይሁን እንጂ ከዚያ አንዳች አትቀምስም” አለው።
የጥበቃውን ሥራ የሚያከናውኑት እነርሱ በመሆናቸው የሚያድሩትም በዚያው በእግዚአብሔር ቤት አካባቢ ነበረ፤ ጧት ጧትም ደጆቹን የሚከፍቱት እነርሱ ነበሩ።
የአባቱን የዳዊትን ሥርዐት በመከተልም፣ ካህናቱን በየአገልግሎት ክፍላቸው ሌዋውያኑንም ምስጋናውን እንዲመሩና በየዕለቱ ሥራቸው ካህናቱን እንዲረዱ መደባቸው። ደግሞም የእግዚአብሔር ሰው ዳዊት ባዘዘው መሠረት፣ የቤተ መቅደሱን በር ጠባቂዎች በልዩ ልዩ በሮች ጥበቃ ላይ በየክፍላቸው መደባቸው።
በሌላ ስፍራ ሺሕ ቀን ከመኖር፣ በአደባባይህ አንዲት ቀን መዋል ይሻላል፤ በክፉዎች ድንኳን ከመቀመጥ ይልቅ፣ በአምላኬ ቤት ደጅ መቆም እመርጣለሁ።
የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ፣ የመልክያን ልጅ ፋስኮርን እንዲሁም የመዕሤያን ልጅ ካህኑን ሶፎንያስን ወደ እርሱ በላከ ጊዜ፣ ቃል ከእግዚአብሔር ወደ ኤርምያስ መጣ፤ የተላኩትም እንዲህ ብለውት ነበር፤
የይሁዳም ባለሥልጣኖች ስለ እነዚህ ነገሮች በሰሙ ጊዜ፣ ከቤተ መንግሥት ወደ እግዚአብሔር ቤት ወጡ፤ በእግዚአብሔር ቤት፣ አዲሱ በር በተባለው መግቢያ ተቀመጡ።
ስለዚህ የካባስን ልጅ የኤርምያስን ልጅ ያእዛንያን፣ ወንድሞቹንና ወንዶች ልጆቹን ሁሉ፣ የሬካባውያንን ወገን በአጠቃላይ ሄጄ ጠራኋቸው፤
የክብር ዘበኞቹ አዛዥም ሊቀ ካህኑን ሠራያን፣ በማዕርግ ከርሱ ቀጥሎ ያለውን ካህኑን ሶፎንያስንና ሦስቱን የበር ጠባቂዎች አስሮ ወሰዳቸው፤
በእያንዳንዱ የውስጥ መግቢያ በር መተላለፊያ በረንዳ አጠገብ የሚቃጠል መሥዋዕት የሚታጠብበት በር ያለው ክፍል አለ።
በእኔና በጣዖታቱ መካከል ግንብ ብቻ ሲቀር፣ መድረኮቻቸውን ከመድረኬ አጠገብ፣ መቃኖቻቸውን ከመቃኖቼ አጠገብ በማድረግ፣ በአስጸያፊ ድርጊታቸው ቅዱስ ስሜን አረከሱ፤ ስለዚህ በቍጣዬ አጠፋኋቸው።
የእግዚአብሔር ሰው ሙሴ ከመሞቱ በፊት ለእስራኤላውያን የሰጠው ቃለ ቡራኬ ይህ ነው፤
የእግዚአብሔር ሰው ሆይ፤ አንተ ግን ከዚህ ሁሉ ሽሽ፤ ጽድቅን፣ እውነተኛ መንፈሳዊ ሕይወትን፣ እምነትን፣ ፍቅርን፣ ትዕግሥትንና ገርነትን ተከታተል።
ይኸውም የእግዚአብሔር ሰው ለመልካም ሥራ ሁሉ ብቁ ሆኖ እንዲገኝ ነው።
የይሁዳም ሰዎች በጌልገላ ወደ ኢያሱ ቀረቡ፤ ከዚያም የቄኔዛዊው የዮፎኒ ልጅ ካሌብ እንዲህ አለው፤ “እግዚአብሔር በቃዴስ በርኔ ስለ አንተና ስለ እኔ፣ የእግዚአብሔር ሰው ለሆነው ለሙሴ የተናገረውን ታውቃለህ።
በዚህ ጊዜ አንድ የእግዚአብሔር ሰው ወደ ዔሊ መጥቶ እንዲህ አለው፤ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘የአባትህ ቤት በግብጽ ምድር በፈርዖን እጅ በነበረ ጊዜ ራሴን ገለጥሁለት?