“ምድርን የፈጠራት፣ ያበጃትና የመሠረታት እግዚአብሔር፣ ስሙ እግዚአብሔር የሆነ፣ እርሱ እንዲህ ይላል፤
እግዚአብሔር ጽዮንን መልሶ ይሠራታልና፤ በክብሩም ይገለጣል።
በርግጥም ስለ ጽዮን፣ “ይህም ያም ሰው በርሷ ውስጥ ተወለዱ፤ ልዑልም ራሱ ያጸናታል” ይባላል።
እግዚአብሔር ተዋጊ ነው፤ ስሙም እግዚአብሔር ነው።
ሁሉን ቻይ አምላክ ሆኜ ለአብርሃም፣ ለይሥሐቅ፣ ለያዕቆብ ተገለጥሁላቸው፤ ነገር ግን እግዚአብሔር በተባለው ስሜ ራሴን አልገለጥሁላቸውም።
ከዚያ ሕዝብ ለሚመጡ መልእክተኞች ምን መልስ ይሰጣል? “መልሱ፣ ‘እግዚአብሔር ጽዮንን መሥርቷል፤ መከራን የተቀበለው ሕዝብም፣ በርሷ ውስጥ መጠጊያን አግኝቷል’ የሚል ነው።”
“ይህን ቀድሞ እንደ ወሰንሁት፣ አልሰማህምን? ጥንትም እንዳቀድሁት አሁን ግን እንዲፈጸም አደረግሁት፤ ይህም የተመሸጉትን ከተሞች አንተ የድንጋይ ክምር ማድረግህ ነው።
“እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ ስሜም ይህ ነው! ክብሬን ለሌላ፣ ምስጋናዬንም ለጣዖት አልሰጥም።
አሁን ግን፣ ያዕቆብ ሆይ የፈጠረህ፣ እስራኤል ሆይ! የሠራህ፣ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ተቤዥቼሃለሁና አትፍራ፤ በስምህ ጠርቼሃለሁ፤ አንተ የእኔ ነህ፤
ለራሴ ያበጀሁት ሕዝብ ምስጋናዬን ያውጅ ዘንድ ይህን አደርጋለሁ።
ኢየሩሳሌምን እስኪያጸናት፣ የምድርም ምስጋና እስኪያደርጋት ዕረፍት አትስጡት።
የያዕቆብ ዕድል ፈንታ የሆነው ግን እንደ እነዚህ አይደለም፤ እርሱ የሁሉ ነገር ፈጣሪ ነውና፤ እስራኤልም የርስቱ ነገድ ነው። ስሙ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ነው።
“ስለዚህ አስተምራቸዋለሁ፤ ኀይሌንና ታላቅነቴን፣ አሁን አስተምራቸዋለሁ፤ እነርሱም ስሜ እግዚአብሔር፣ እንደ ሆነ ያውቃሉ።
ፍቅርና ቸርነትን ለእልፍ አእላፍ ታሳያለህ፤ ይሁን እንጂ የአባቶችን በደል ከእነርሱ በኋላ በሚነሡ ልጆቻቸው ጕያ ትመልሳለህ፤ ስምህ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር የሆነ፣ ታላቅና ኀያል አምላክ ሆይ፤
ሰባቱን ከዋክብትና ኦሪዮንን የሠራ፣ ጨለማውን ወደ ንጋት ብርሃን የሚለውጥ፣ ቀኑን አጨልሞ ሌሊት የሚያደርግ፣ የባሕሩንም ውሃ ጠርቶ፣ በገጸ ምድር ላይ የሚያፈስስ፣ ስሙ እግዚአብሔር ነው፤
መኖሪያውን በሰማይ የሚሠራ፣ መሠረቱንም በምድር የሚያደርግ፣ የባሕርን ውሃ የሚጠራ፣ በምድርም ገጽ ላይ የሚያፈስስ፣ እርሱ ስሙ እግዚአብሔር ነው።
ምክንያቱም መሠረት ያላትን፣ እግዚአብሔር የሠራትንና የፈጠራትን ከተማ ይጠባበቅ ነበር።
አሁን ግን ከዚህ የሚበልጠውን ሰማያዊ አገር ይናፍቃሉ፤ ስለዚህ እግዚአብሔር አምላካቸው ተብሎ ሊጠራ አላፈረም፤ ከተማን አዘጋጅቶላቸዋልና።
በመንፈስም ወደ አንድ ትልቅና ረዥም ተራራ ወስዶኝ፣ ቅድስቲቱ ከተማ ኢየሩሳሌም ከሰማይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ስትወርድ አሳየኝ።
ቅድስቲቱ ከተማ፣ አዲሲቱ ኢየሩሳሌም ለባሏ እንደ ተዋበች ሙሽራ ተዘጋጅታ ከሰማይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ስትወርድ አየሁ።