ኤርምያስም “የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ አለ፦
ኦርናም፣ “ንጉሥ ጌታዬ ወደ አገልጋዩ የመጣው ለምንድን ነው?” አለ። ዳዊትም መልሶ፣ “መቅሠፍቱ ከሕዝቡ እንዲከለከል ለእግዚአብሔር መሠዊያ እንድሠራ ዐውድማህን ልገዛ ነው” አለው።
ሴዴቅያስንም ወደ ባቢሎን ይወስደዋል፤ በፍርዴ እስከምጐበኘውም ድረስ በዚያ ይቈያል፤ ይላል እግዚአብሔር፤ ከባቢሎናውያን ጋራ ብትዋጉ አይሳካላችሁም” ይላል’ ትላለህ።”
የአጎትህ የሰሎም ልጅ አናምኤል ወደ አንተ መጥቶ፣ ‘የመቤዠት መብት የአንተ ስለ ሆነ፣ በዓናቶት ያለውን መሬቴን ግዛኝ’ ይልሃል።